የወደቁትን እናንሣጕብኝት ባደረግንበት ወቅት እንዳስተዋልነው በማኅበሩ እየተጦሩ ከሚገኙ ወገኖች መካከል አንዳንዶቹ የአብነት መምህራን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ በመንግሥትና በግል ድርጅቶች ሓላፊነት የነበራቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያንና የአገር ባለውለታዎች በሕመም፣ በጤና እና በእርጅና ምክንያት የአልጋ ቁራኛ፣ የደዌ ዳኛ ኾነው ጎዳና ላይ በወደቁበት ወቅት ይህ ማኅበር ደርሶላቸው አስፈላጊውን ዅሉ ድጋፍ እያደረገላቸው ይገኛል፡፡ በተለይ የአእምሮ ሕሙማንና ከአንድ በላይ በኾነ የጤና እክል የተጠቁ ማለትም የማየትም የመስማትም የመንቀሳቀስም ችግር ያለባቸውና ሰውነታቸውን መቈጣጠር የማይችሉ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እኅቶች ኹኔታ ልብን ይነካል፡፡ እነዚህ ወገኖች የሚንቀሳቀሱትም፣ የሚመገቡትም፣ የሚለብሱትም፣ የሚጸዳዱትም በሰው ርዳታ ነው፡፡ እነርሱን ያየ ሰው የማኅበሩን ዓላማ በግልጽ ይረዳዋል የሚል እምነት አለን፡፡ Read more http://eotcmk.org/a/wp-content/uploads/logo-4.png 0 0 Mahibere Kidusan http://eotcmk.org/a/wp-content/uploads/logo-4.png Mahibere Kidusan2017-08-16 07:14:282017-11-07 07:56:11የወደቁትን እናንሣ
የበረዶ ናዳ በገዳመ ናዳየገዳሙ ደን እና ፍራፍሬ በበረዶ ናዳ ቢወድምም ዋና አስተዳዳሪው እና ማኅበረ መነኮሳቱ ብሩህ ፊታቸው አልቀዘቀዘም፡፡ ጉባኤ ቤቱም አልተፈታም፡፡ ገዳማውያኑ በተለመደው መንፈሳዊ ቋንቋ ‹‹እግዚአብሔር ይመስገን! ደኅና ነን … በአትክልት ላይ እንጂ በሰውና በእንስሳት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም … ዅሉም ነገር ለበጎ ነው … ከዚህ የባሰ አያምጣ …›› እያሉ እነርሱን ለመጠየቅና ጉዳን ለማየት የሚመጡ ምእመናንን ያረጋጋሉ፡፡ ገዳማውያን እንዲህ ናቸው፤ ተበድለው እንዳልተበደሉ፤ ተጎድተው እንዳልተጎዱ፤ ተቸግረው እንዳልተቸገሩ በማመን በኾነው ነገር ዅሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፡፡ በዚህ ዓመት በፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም ገዳም እና በአካባቢው በወርኃ ሰኔ የደረሰው ጉዳት እግዚአብሔርን ወደማማረር የሚገፋፋ ከባድ ፈተና ቢኾንም የገዳሙ አባቶች እና እናቶች ግን እግዚአብሔርን ማመስገናቸውን ለቅጽበት አላቋረጡም ነበር፡፡ በስበብ አስባቡ እግዚአብሔርን ና ውረድ የምንል ምእመናን ከእነርሱ ትምህርት ልንወስድ ይገባል፡፡ Read more http://eotcmk.org/a/wp-content/uploads/logo-4.png 0 0 Mahibere Kidusan http://eotcmk.org/a/wp-content/uploads/logo-4.png Mahibere Kidusan2017-08-07 17:13:122017-08-18 19:51:55የበረዶ ናዳ በገዳመ ናዳ
አርአያነት ያለው ተግባር በአዳማ ማእከልአገልግሎቱን በአግባቡ ለመስጠት እንዲቻል ልዩ ልዩ ድጋፍ ላደረጉ የመንግሥት ተቋማትና የሥራ ሓላፊዎች፤ ለበጎ አድራጊ ምእመናንና በአገልግሎቱ ለተሳተፉ ወገኖች ዅሉ ሰብሳቢው በማኅበሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ እኛም እንደ ዝግጅት ክፍል የቤተ ክርስቲያናችንን መንፈሳዊ ተልእኮ ይበልጥ ለማጉላት፤ የአገራችንን ስም በመልካም ጎን ለማስጠራት ይቻል ዘንድ አዳማ ማእከል ከላይ የተጠቀሱትንና እነዚህን የመሰሉ አርአያነት ያላቸው ተግባራቱን አጠናክሮ ቢቀጥል፤ የሌሎች ማእከላት፣ የሰንበት ት/ቤቶች እና የማኅበራት አባላትም ይህን የማእከሉን ፈለግ ቢከተሉ መልካም ነው እንላለን፡፡ Read more http://eotcmk.org/a/wp-content/uploads/logo-4.png 0 0 Mahibere Kidusan http://eotcmk.org/a/wp-content/uploads/logo-4.png Mahibere Kidusan2017-06-15 14:59:462018-03-29 09:10:41አርአያነት ያለው ተግባር በአዳማ ማእከል
የወደቁትን እናንሣ
ጕብኝት ባደረግንበት ወቅት እንዳስተዋልነው በማኅበሩ እየተጦሩ ከሚገኙ ወገኖች መካከል አንዳንዶቹ የአብነት መምህራን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ በመንግሥትና በግል ድርጅቶች ሓላፊነት የነበራቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያንና የአገር ባለውለታዎች በሕመም፣ በጤና እና በእርጅና ምክንያት የአልጋ ቁራኛ፣ የደዌ ዳኛ ኾነው ጎዳና ላይ በወደቁበት ወቅት ይህ ማኅበር ደርሶላቸው አስፈላጊውን ዅሉ ድጋፍ እያደረገላቸው ይገኛል፡፡ በተለይ የአእምሮ ሕሙማንና ከአንድ በላይ በኾነ የጤና እክል የተጠቁ ማለትም የማየትም የመስማትም የመንቀሳቀስም ችግር ያለባቸውና ሰውነታቸውን መቈጣጠር የማይችሉ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እኅቶች ኹኔታ ልብን ይነካል፡፡ እነዚህ ወገኖች የሚንቀሳቀሱትም፣ የሚመገቡትም፣ የሚለብሱትም፣ የሚጸዳዱትም በሰው ርዳታ ነው፡፡ እነርሱን ያየ ሰው የማኅበሩን ዓላማ በግልጽ ይረዳዋል የሚል እምነት አለን፡፡
የበረዶ ናዳ በገዳመ ናዳ
የገዳሙ ደን እና ፍራፍሬ በበረዶ ናዳ ቢወድምም ዋና አስተዳዳሪው እና ማኅበረ መነኮሳቱ ብሩህ ፊታቸው አልቀዘቀዘም፡፡ ጉባኤ ቤቱም አልተፈታም፡፡ ገዳማውያኑ በተለመደው መንፈሳዊ ቋንቋ ‹‹እግዚአብሔር ይመስገን! ደኅና ነን … በአትክልት ላይ እንጂ በሰውና በእንስሳት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም … ዅሉም ነገር ለበጎ ነው … ከዚህ የባሰ አያምጣ …›› እያሉ እነርሱን ለመጠየቅና ጉዳን ለማየት የሚመጡ ምእመናንን ያረጋጋሉ፡፡ ገዳማውያን እንዲህ ናቸው፤ ተበድለው እንዳልተበደሉ፤ ተጎድተው እንዳልተጎዱ፤ ተቸግረው እንዳልተቸገሩ በማመን በኾነው ነገር ዅሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፡፡ በዚህ ዓመት በፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም ገዳም እና በአካባቢው በወርኃ ሰኔ የደረሰው ጉዳት እግዚአብሔርን ወደማማረር የሚገፋፋ ከባድ ፈተና ቢኾንም የገዳሙ አባቶች እና እናቶች ግን እግዚአብሔርን ማመስገናቸውን ለቅጽበት አላቋረጡም ነበር፡፡ በስበብ አስባቡ እግዚአብሔርን ና ውረድ የምንል ምእመናን ከእነርሱ ትምህርት ልንወስድ ይገባል፡፡
አርአያነት ያለው ተግባር በአዳማ ማእከል
አገልግሎቱን በአግባቡ ለመስጠት እንዲቻል ልዩ ልዩ ድጋፍ ላደረጉ የመንግሥት ተቋማትና የሥራ ሓላፊዎች፤ ለበጎ አድራጊ ምእመናንና በአገልግሎቱ ለተሳተፉ ወገኖች ዅሉ ሰብሳቢው በማኅበሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ እኛም እንደ ዝግጅት ክፍል የቤተ ክርስቲያናችንን መንፈሳዊ ተልእኮ ይበልጥ ለማጉላት፤ የአገራችንን ስም በመልካም ጎን ለማስጠራት ይቻል ዘንድ አዳማ ማእከል ከላይ የተጠቀሱትንና እነዚህን የመሰሉ አርአያነት ያላቸው ተግባራቱን አጠናክሮ ቢቀጥል፤ የሌሎች ማእከላት፣ የሰንበት ት/ቤቶች እና የማኅበራት አባላትም ይህን የማእከሉን ፈለግ ቢከተሉ መልካም ነው እንላለን፡፡