ሆሣ ርያም

በመዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል

መጋቢት ፳፰፤፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

በጌታ ስም የሚመጣ

ከምርኮ አገር ከባርነት የሚያወጣ

ብሩክ ቅዱስ የአበው ተስፋ

የመርገም ጨርቅ ባንተ ጠፋ

የነቢያት ትንቢት የጽድቃቸው ዜና

የሕይወት እንጀራ የእስራኤል መና

ቃል ከሥጋ ጋራ በተዋሕዶ ጸና

በሰማያት የምትኖር የተጋረድክ በደመና

በምድር ላይ ተመላለስክ ታየህ በጎዳና

አላዋቂ  በማስተዋሉ ተደገፈ በጥበቡ አመነ

የዚህ ዓለም እውቀት ግን ከንቱ ሆነ

በማኅበር በጉባኤ መካከል ተገለጠ

የዋህ ሆኖ የጽዮን ልጅ በአህያ ላይ ተቀመጠ

ከሕፃናት ከሚጠቡ አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ

ከንፈሮቻችንን ለምስጋና አንደበታችንን ለዝማሬ ከፈትህ

እኛም ልጆችህ ይዘን ዝንጣፊ ዘንባባ

በሐሴት ተመልተን አሸብርቀን እንደ አበባ

የሰላም ንጉሥ መድኃኔዓለም

ስለ ስምህ ተቀኝተናል ሆሣዕና በአርያም!