• እንኳን በደኅና መጡ !

“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ “ (ኤፌ ፭፥፲፮)

አዲሱ ዓመትን ለመሸጋገር በነፍስ ወከፍ አሰፍስፈንናል ምኑን ጥለን ምኑን አንጠልጥለን እንደምንሸጋገር ግን ብዙዎቻችን አናውቅም፤ ምናልባት ጥቂቶች ለባውያን (ልባሞች) ያውቁ ይሆናል ይህም ሲባል ባለፈው ዘመን ካከናወኑት ተግባር መካከል ወደ ኋላ የጎተታቸውንና ከዘመን ጋር ያጋጫቸውን ክፉ ነገር ትተው ወደ ፊት እንዲራመዱ ያደረጋቸውንና ከዘመን ጋር ያፋቀራቸውን ደግ ደጉን ይዘው መሸጋገርን ማለት ነው፡፡  ወይም ባለፈው ዘመን ከክፉ ሥራና ከስንፍና […]

 ሱባኤ

ቀሲስ ኃይለሚካኤል ብርሃኑ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የጽሞና ጊዜያት ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ ሱባኤ  ነው፡፡ ሱባኤ  በሰዋስው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ይኸውም የሚፈጸመውን የጾም ወቅት በቀናት፣ በሳምንታት እና በወራት በመወሰን የአንድ ሱባኤ ልክ ሰባት ቀን ሆኖ የሚፈጸምበት ሥርዓት ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ ትውፊት መሠረት ሰባት ቁጥር የፍጹምነት መገለጫ ነው፡፡ በተለይም የኦሪትን ሕግ በሙሴ አማካኝነት በተቀበሉት […]

መልካም ዕውቀት ሞገስን ይሰጣል

ለሰው ልጆች ከተሰጡ ጸጋዎች አንዱ ዕውቀት ነው፡፡ የሰው ልጅ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አዲስ ነገርን የመልመድ፣ አካባቢውን የማጥናትና መገንዘብን  እያዳበረ አካባቢውን ከመልመድ አልፎ በዕውቀት እየጎለመሰ፣ ጥሩውንና መጥፎውን እየለየ ያድጋል፡፡ መልካም የሆነውን መንገድ ለሚከተሉና እንደ እግዚአብሔር ቃል ለሚመላለሱት ዕውቀትና ጥበብን ያሳድርባቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “የምድር ገዢዎች ሆይ ጽድቅን ውደዷት፤ የእግዚአብሔርንም ኃይል በበጎ ዕውቅት አስቡት፣ በቅን ልቡናም ፈልጉት” ይለናል፡፡(ጥበ.፩፥፩)፡፡ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን