• እንኳን በደኅና መጡ !

ጌታችን ኢየሱስ ተወለደ

ዲያቆን አለልኝ ጥሩዬ ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን በዓለም ላይ ሠልጥኖ የነበረውን ጨለማ ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ሰው ሆነ፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አማናዊው ብርሃን ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው እንዳለው ‹‹ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኵሉ ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም፤ በጨለማ ውስጥ ለሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው››  (ኢሳ. ፱፥፪)፡፡ ቀዳሚ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ […]

ራስን መግዛት

በመ/ር በትረ ማርያም አበባው(የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፈተ መነኮሳት መምህር) ራስን መግዛት ማለት ራስን ከክፉ ነገር መጠበቅ፣ ሰውነትን መቆጣጠር፣ ራስን ከኃጢኣት ማራቅ ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ ራስን መግዛት የመንፈስ ፍሬ እንደሆነ ገልጧል። (ገላ. ፭፥፳፪) ቅዱስ ጴጥሮስም በ(፪ኛ ጴጥ.፩፣፮) “በበጎነትም ዕውቀትን በዕውቀትም ራስን መግዛትን ራስንም በመግዛት መጽናትን በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችነትን መዋደድ […]

ከፊት ይልቅ ትጉ (፪ኛ.ጴጥ. ፩፥፲)

በመጋቤ ሃይማኖት መ/ር  ምትኩ አበራ ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡ ኃይለ ቃሉን የምናገኘው ደግሞ በ፪ኛ ጴጥ.፩፥፭-፲፩ ላይ ነው፡፡ ሙሉው ንባብ እንዲህ ይላል፡- “… ስለዚህ ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፤ በበጎነትም ዕውቀትን፤ በዕውቀትም ራስን መግዛት፤ ራስንም በመግዛት መጽናትን፤ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፤ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፤ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ፤ እነዚህ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን