• እንኳን በደኅና መጡ !

“…ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ ”(ዮሐ.፫፥፩)

 በቀሲስ ኃይለሚካኤል ብርሃኑ የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሌሊት ወደ እርሱ እየመጣ ይማር ለነበረው  ኒቆዲሞስ ለተባለ ፈሪሳዊ ሰው የዳግም ልደትን ምሥጢር (ምሥጢረ ጥምቀትን) ያስተማረበት በመሆኑ ኒቆዲሞስ ተብሏል፡፡ ኒቆዲሞስ በሕይወት ዘመኑ ቅንናና መልካም ሰው እንደነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቀን ለመገናኘት ሁኔታው ባይፈቅድለትም በሌሊት እየመጣ የሕይወት ቃል በመማር ያልገባውንም በመጠየቅ ያሳየው […]

የኒቆዲሞስ መንፈሳዊ ዕድገት

ኤልያስ ገ/ሥላሴ አሐቲ፣ ቅድስት፣ ኵላዊት እና ሐዋርያዊት የሆነችው ቤተክርስቲያናችን እኛ ምእመኖቿ በዓለም ሐሳብ ድል እንዳንነሣ፣ ይልቅስ ፍትወታትን ሁሉ ድል አድርገን ራሳችንን ገዝተን (ተቈጣጥረን) በውስጣችን ፈቃደ እግዚአብሔርን አንግሠን ምድራዊውን ሳይሆን ሰማያዊውን እያሰብን እንድንኖር በዓመቱ ውስጥ በተለያዩ ወራት የሚጾሙ አጽዋማትን ሠርታልናለች፡፡ ከነዚህ አጽዋማት ውስጥ አንዱና ዋነኛው ደግሞ አሁን በዚህ ወቅት እየጾምነው ያለነው ዐቢይ ጾም ነው፡፡ ዐቢይ ጾም […]

“ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ”(ኢዩ.፪፥፲፫)

በእንዳለ ደምስስ ይህንን ቃል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩኤል ላይ አድሮ ልባቸው ለደነደነና ኃጢአት በመሥራት ለሚተጉት አይሁድ የተናገረው ተግሣጽ ነው፡፡ እግዚአብሔር በባሕርይው ታጋሽ፣ ሁሉን ቻይ ሲሆን ስለ በደላቸው ብዛት ማጥፋት ሲችል ይመለሱ ዘንድ ከመካከላቸው ነቢያትን እያስነሣ ሲገስጻቸው እንመለከታለን፡፡ ስለ ኃጢአታቸው ተጸጸተው  ወደ እርሱ ለሚጮኹ፣ ልብሳቸውን ሳይሆን ልባቸውን ለሚቀዱ ራሳቸውን ለአምላካቸው አሳልፈው ለሚሠጡ ደግሞ ምሕረቱ ቅርብ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን