• እንኳን በደኅና መጡ !

“ሠናይ ውእቱ ለነ ሀልዎ ዝየ” (ማቴ.፲፯፥፬)

በዲ/ን ዐቢይ ሙሉቀን የቃሉ ተናጋሪ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። ቃሉን የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን ሊገልጥላቸው ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን፣ ከሐዋርያት ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ወደ ተራራው ባወጣቸው ጊዜ ነው፡፡ ሙሴና ኤልያስ ከክርስቶስ ጋር ሲነጋገሩ ሰምቶ “በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፣ ብትፈቅድስ ሦስት ሰቀላዎች እንሥራ አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ” በማለት […]

ሱባኤያችን በረከት የሚያሰጥ ይሁን

በእንዳለ ደምስስ በረከትን በመሻት በፍልሰታ ለማርያም ጾም ሱባኤ ለመያዝ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በታነጸውና በቤተ ክርስቲያናችን ከሚታወቁ ታላላቅ ገዳማት ወደ አንዱ ለመሔድ ዝግጅት ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ ወደ ንስሓ አባቴ ቀርቤ ንስሓ ገብቼና ቀኖናዬን ተቀብዬ፣ ከመሥሪያ ቤቴ ደግሞ ፈቃድ ቀኑ ሲደርስ በዋዜማው የሚያስፈልጉኝን የጸሎት መጻሕፍት፣ አልባሳት፣ በሶና ጥሬ ሽምብራ በቦርሳዬ ሸክፌ፣ የጸበል መቅጃ አነስተኛ ጀሪካን አንጠልጥዬ […]

“በዐዋቂ ልጅ ሀገር ትጸናለች” (ሲራ.፲፮፥፬)

የአንድ ሀገር ቋሚ ሀብቶቿ ልጆችዋ ናቸው፡፡ ሕዝብ ሀገር ወዳድና ጠንካራ ሲሆን አነዋወሩን ከመቀየር ጀምሮ የሀገሩን ታሪክ በወርቃማ ቀለም መጻፍ ይችላል፡፡ እንዲህ ያለው ተስፋ ብዙውን ጊዜ በአዳጊ ሀገሮች ለወጣቶች ይሰጣል፡፡ ይህ የሚሆነው በብዙ ሀገሮች ውስጥ ከፍተኛውን የነዋሪ ቁጥር ከሚይዙት ውስጥ ሕፃናትና ወጣቶች በመሆናቸው እና በአባቶች ፈንታ አገር የሚረከቡም ጭምር በመሆናቸው ነው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም ይህን ከፍተኛ ቁጥር […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን