የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ጥናታዊ ጽሑፎች በማቅረብ ቀጥሏል

የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ሐምሌ ፳፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች ሰዓታቸውን ጠብቀው እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በጸሎተ ወንጌል የተጀመረው መርሐ ግብር የማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን ያሬዳዊ መዝሙር በማቅረብ ቀጥሎ “ዕውቀት የሕይወት ምንጭ ነው” (ምሳ. ፲፮፥፳፪) በሚል ርእስ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ያስተማሩ ሲሆን፤ ዲ/ን ዋሲሁን በላይ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ “የማኅበረ ቅዱሳን ታሪክ፣ አገልግሎትና ፈተናዎች ከ፲፱፻፹፬-፳፻፲፬ ዓ.ም” በሚል ሰፋ ያለ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡

በጥናታቸውም ለማኅበረ ቅዱሳን መመሥረት ምክንያት የሆኑትን መሠረታዊ ጉዳዮችና ሂደቱን፣ ያለፉትን የ፴ ዓመታት አገልግሎት፣ እንዲሁም ያጋጠሙ ፈተናዎችንና ፈተናዎቹን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶችንም ዳስሰዋል፡፡ ጥናታዊ ጽሑፉ ከቀረበ በኋላም ተሳታፊዎች ላነሷቸው ጥያቄዎች በአቶ ግዛቸው ሲሳይ የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ሰብሳቢ እና ጥናቱን ባቀረቡት ዲ/ን ዋሲሁን በላይ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የጉባኤው የጠዋቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *