ማኅበረ ቅዱሳን የባለ ዕድለኞች ዕጣ ቁጥሮችን ይፋ አደረገ
ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያትን አገልግሎትን ለማጠናከር ይረዳው ዘንድ “ዘመኑን የዋጀ ንቁ ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን” በሚል መሪ ቃል ለአባላት፣ ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎችና አገልግሎቱን ለሚደግፉ ምእመናን ሲያሠራጭ የቆየው ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም፣ ወደ ግብጽና ወደ ኢትዮጵያ ገዳማት መንፈሳዊ ጉብኝትን ጨምሮ ሌሎችንም ዕድሎችን የሚያስገኙት የበረከት የዕጣ ቁጥሮች በቴክኖሎጂ በታገዘ የዕጣ አወጣጥ መርሐ ግብር ታዛቢዎችና ምእመናን በተገኙበት ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፳፻፲፰ ዓ.ም ይፋ አደረገ፡፡
በዕጣ አወጣጥ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ ባስተላለፉት መልእክት “ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በተሻለ ጥራትና አቅም ለማስተማር ብቻውን ሳይሆን የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የመምህራንና የምእመናን ትብብርና ድጋፍ ሳይለየው የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በተሻለ ጥራትና አቅም አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል” በማለት የገለጹ ሲሆን የበረከት ዕጣ ትኬቱን በማሠራጨት ሂደት ውስጥ የተሳተፉትን ሁሉ አመስግነዋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አበበ በዳዳ የበረከት ዕጣ ትኬቱ የተዘጋጀበት ምክንያትና ሂደቱን በተመለከተ ባስተላለፉት መልእክት “ማኅበረ ቅዱሳን ከ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ጀርሮ በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ፈቃድና ኃላፊነት መሠረት የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን ለማስተማር መምህራንን በመመደብ፣ መማሪያ ቦታን በማዘጋጀት፣ በንስሓ አባቶች አማካይነት ሕይወታቸውን በመንፈሳዊ መንገድ እንዲመሩ በማድረግ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኦርቶዶክሰውያን ተማሪዎችን በማፍራት አስመርቋል፡፡ “በዚህም አገልግሎት ተማሪዎች ለራሳቸው፣ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ አገልግሎት እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡” ብለዋል፡፡
አቶ አበበ አያይዘውም “ማኅበረ ቅዱሳን ከ፲፱፩፺፮ ዓ.ም ጀምሮም ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ ሲያስተምር በየጊዜው የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም በ፳፻፮ ዓ.ም በዓለማችን፣ በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያን በሚታዩ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች፣ የሰ/ት ት/ቤቶች ከ፳፻፲፩ ዓ.ም ጀምሮ ሥርዓተ ትምህርት መዘጋጀት፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከ፳፻፲፮ ዓ.ም የተቋማዊ ለውጥ ትግበራ መጀመርና የመንግሥት የትምህርት ፖሊሲ መቀያየር ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዐሥር ዓመታት በኋላ በ፳፻፲፯ ዓ.ም ለግቢ ጉባኤያት ሲሰጠው የነበረውን ሥርዓተ ትምህርት ከግምት ውስጥ በማስገባት መከለስ ችሏል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
“እነዚህም ምክንያቶችን መሠረት በማድረግ ፲፬ የትምህርት ዓይነቶች የተዘጋጁ ሲሆን ለኅትመት፣ የመምህራንን አቅም፣ ጥራትና ቁጥር ለማሳደግ፣ የመማሪያ ቦታ ችግሮችን ለመቅረፍና የሥልጠና መስጫ መእከል ለመገንባት ታስቦ የበረከት ዕጣው ተዘጋጅቷል” በማለት አብራርተዋል፡፡
በበረከት ዕጣ ትኬቱ አቅማቸውን ሁሉ በመጠቀም ድጋፍ ላደረጉና በማሠራጨት ለተባበሩት አካላት ሁሉ ምስጋና በማቅረብ የዕጣ መውጣት መርሐ ግብሩ እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
፩ኛ ዕጣ፡- 409652፡- ወደ ኢየሩሳሌሌም ገዳማት ጉዞ ለ፯ ቀናት፣
፪ኛ ዕጣ፡- 309903፡- ወደ ግብጽ ገዳማት መንፈሳዊ ጉብኝት ለ፯ ቀናት፣
፫ኛ ዕጣ፡- 076840፡- ወደ ኢትዮጵያ ገዳማት ወደ አንዱ ከአንድ ቤተሰብ ጋር መንፈሳዊ ጉብኝነት በአውሮፕላን ለ፭ ቀናት፣
፬ኛ ዕጣ፡- 366930፡- ወደ ኢትዮጵያ ገዳማት መንፈሳዊ ጉብኝት ከሁለት ቤተሰብ ጋር በየብስ ትራንስፖርት ለ፯ ቀናት፣
፭ኛ ዕጣ፡- 160582፡- ላፕቶፕ ኮምፐዩተር core i7 10Th G የሚያስገኘው የዕጣ ቁጥር፣
፮ኛ ዕጣ፡- 201414፡- ላፕቶፕ ኮምፒዩተር core i5 የሚያስገኘው የዕጣ ቁጥር፣
፯ኛ ዕጣ፡- 478450፡- ሳምሰንግ ታብሌት ጋላክሲ (Samsung Galaxy tablet A8 10.5) ሆነው ወጥተዋል፡፡
በተጨማሪም ፳፩ የዳረጎት ዕጣዎች የወጡ ሲሆን ዐሥር የዕጣዎች እያንዳንዳቸው የሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ፤ እንዲሁም አሥራ አንድ ዕጣዎች እያንዳንዳቸው መዝሙረ ዳዊት የሚያስገኙ ሆነው ወጥተዋል፡፡
በዚህም መሠረት የሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስገኙት ዕጣዎች፡-
- 373427
- 360509
- 345974
- 249715
- 263391
- 435703
- 320085
- 394074
- 315800
- 232590
ዐሥራ አንድ የመዝሙረ ዳዊት የጸሎት መጽሐፍ የሚያስገኙት ዕጣዎች፡-
- 374223
- 354749
- 247657
- 265287
- 317331
- 435060
- 319033
- 291453
- 179959
- 259285
- 244216 ሆነው ወጥተዋል፡፡

Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!