፲፪ኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር በመካሄድ ላይ ይገኛል

፲፪ኛው የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር በዛሬው ዕለት ሐምሌ ፳፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም ከመላው ዓለም ከሚገኙ የማኅበሩ ማእከላትና ግቢ ጉባኤያት የተውጣጡ ከ፫፻ በላይ ተወካዮች በተገኙበት በማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ ፫ኛው ወለል ላይ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ ጉባኤው በጽሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን አቶ ግዛቸው  ሲሳይ የማኅበሩ ምክትል ሰብሳቢ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ ቀጥሏል፡፡ አቶ ግዛቸው ባስተላለፉት መልእክትም “በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ እየተገናኝን ስለ አገልግሎታችን የምንመካከርበት፣ መልካም ሥራዎቻችንን የምናስቀጥልበት፣ እንዲሁም ደግሞ ድክመታችንን የምናርምበትና ወደ ተጠናከረ አገልግሎት እንድንሸጋገር ከሌሎች ወንድሞቻችንንና እኅቶቻችን ልምድ የምቀስምበት ጉባኤ ነው” ብለዋል፡፡

ጉባኤችው ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በውጭ ሀገራት የሚገኙ የማኅበሩ ተወካዮች በቀጥታ ሥርጭት በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *