- የመጀመሪያውየግቢ ጉባኤያት ተወካዮች ሀገር ዐቀፍ ሴሚናር ከየካቲት ፲፫-፲፬ ቀን በ፲፱፺፩ ዓ.ም ተከናወነ፡፡
- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት ሲማሩ የቆዩ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመጀመሪዋ የደረቅ ቅጅ /Hard copy/ የምረቃ መጽሔት በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ተዘጋጀ፡፡
- የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቃና ጋዜጣ ቁጥር ፩ የካቲት ፳፻ ዓ.ም መታተሟና ዋጋዋም ፩ ብር ከ፳፭ ሣንቲም የነበረ ሲሆን የገጽ ብዛቱም ፰ ነበር፡፡
- ማኅበረ ቅዱሳን በሀገር ውስጥ ፬፻፳፱ እና ፳፫ በውጭ ሀገራት ግቢ ጉባኤያትን እያስተማረ ይገኛል፡፡
- በሀገር ወስጥ ፪፻፹፮፣ በውጭ ሀገራት ፲፯ የጸደቁ ግቢ ጉባኤያት እና በሀገር ውስጥ ፻፵፭ በክትትል ላይ ያሉ፣ በውጭ ሀገራት ደግሞ ፮ ግቢ ጉባኤያት ይገኛሉ፡፡
- ማኀበረ ቅዱሳን በአጠቃላይ ፬፻፶፬(፬፻፴፩ በሀገር ውስጥ እና ፳፫ በውጭ ሀገራት) ግቢ ጉባኤያትን እያስተማረ መሆኑን ያውቃሉ?
- የመጀመሪያው የግቢ ጉባኤያት የተከታታይ ትምህርት /course/ ማስተማሪያ መጻሕፍት ዝግጀት የተጀመረው በ፲፱፻፺፮ ዓ.ም ነበር፡፡ በተቀረጸው ሥርዓተ ትምህርት /carricullum/ ውስጥ ፳፪ የተከታታይ ትምህርት መጻሕፍትን በማዘጋጀት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ነገረ ሃይማኖት ማስተማሩን ቀጠለ፡፡
- በ፳፻፭ ዓ.ም የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ በማድረግ የትምህርት ዓይነቶቹን ወደ ፲፩ ዝቅ በማድረግ እስከ አሁን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
- ከ፳፻፲፩ ዓ.ም ባሉት ዓመታት የምረቃ መጽሔትን ከወረቀት ኀትመት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወደሚታገዝ (Digital) አሠራር እንዲቀየር ስምምነት መደረሱን እና ከ፳፻፲፪ ዓ..ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወደሚታገዝ (Digital) አሠራር ተቀየረ፡፡
- ማኅበሩ በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም በክረምቱ ወራት ለተተኪ መምህራን በአማርኛ ሥልጠና መስጠት ሲጀምር፣ ከ፲፱፻፺፯ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአፋን ኦሮሞ መስጠት ቀጠለ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአፋን ኦሮሞ ማስተማር የሚችሉ መምህራንን ማፍራት ችሏል፡፡
- ማኅበረ ቅዱሳን ከየካቲት ፳፻ ዓ.ም ጀምሮ በተለይ ለግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች “ጉባኤ ቃና” የተሰኘ መጽሔት በየ፫ ወሩ በአማርኛ እንዲሁም በአማርኛ የተዘጋጀው መጽሔት ወደ አፋን ኦሮሞ በመተርጎም አዘጋጅቶ ማሠራጨት ጀመረ፡፡
- ማኅበሩ ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ በአባቶች ቡራኬ የሚያስመርቃቸው ኦርቶዶክሳውያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ፣ ከ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ቢሆኑም ከኦሮምያ ክልል የሚመጡት በሃይማኖታቸው እንዲጸኑና ከተለያዩ አካላት የሚደረግባቸውን ጫና መቋቋም እንዲችሉ በማሰብ ለሁሉም የሚታተመው የምረቃ መጽሔት በልዩ ሁኔታ በአፋን ኦሮሞ ጭምር ተተርጉሞ እንዲታተም እየተደረገ መሆኑን ያውቃሉ?
https://eotcmk.org/gibi-a/wp-content/uploads/main-header-am-gibi-1.png
0
0
Gibi Gubayeat
https://eotcmk.org/gibi-a/wp-content/uploads/main-header-am-gibi-1.png
Gibi Gubayeat2023-05-11 09:59:512023-05-11 10:05:23ይህን ያውቃሉ?
“የሕይወት ቀን” በግቢ ጉባኤያት“እየባረካቸው ራቃቸው” (ሉቃ. ፳፬፥፶፩)
Scroll to top
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!