የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር የከሰዓት በኋላ ውሎ

የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ከሰዓት በኋላ ውሎው የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዾ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተገኙ ሲሆን መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡ በመልእክታቸውም ትምህርት ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን መያዝ እንዳለበትም ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም፡-  ትምህርት መንፈሳዊ ሀብት መሆኑ፤ ትምህርት ብርሃን እንደሆነ፤ እንዲሁም ትምህርት የማያልቅ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

“ትምህርት መንፈሳዊ ሀብት ነው ስንል አይሰረቅም፣ አይወሰድም፣ አይሞትም፣ ለሌላው የሚያካፍሉትና የሚቀጥል ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ብፀዕነታቸው የትምህርት ብርሃንነትን ሲገልጹም “ትምህርት ብርሃን ነው፡፡ ፊትህን፣ ጎንህን፣ ኋላህን እንድታይና እንድታስተውል ነው የሚያደርገው፡፡ ዕውቀታቸውን በመንፈሳዊው የሕይወት ጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎች ብሩሀን ናቸው” ሲሉ የትምህርትን ብርሃንነት ጠቅሰዋል፡፡

ብፁዕነታቸው መንፈሳዊው ትምህርት የማያልቅ መሆኑን ሲያብራሩም “መንፈሳዊ ትምህርት አይልቅም፤ እግዚአብሔርንም አጥንተን አንጨርሰውም፡፡ ትምህርት ትዕግሥትን፣ ጊዜን፣ … ይጠይቃል” በማለት በሴሚናሩ ላይ ለተሳተፉ በግቢ ጉባኤ ለተማሩና ተምረው ለወጡ ወጣቶች በተማሩት ትምህርት መንፈሳዊነታቸውን ጠብቀው በቅንነትና በዕውቀት ላይ ተመርኩዘው እንዲያገለግሉ አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

ከብፁዕ አባታችን ምክርና ቡራኬ በኋላ ጥናታዊ ጽሑፎቸ መቅረባቸው የቀጠሉ ሲሆን “የሕይወት ክህሎት” በዶ/ር ወሰን አራጋው፤ እንዲሁም “የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት መልካም ዕድሎች እና ፈተናዎች” በሚል በዲ/ን ብርሃኑ ታደሰ በተከታታይ ቀርበዋል፡፡

ሴሚናሩ እስከ ምሽት የሚቀጥል ሲሆን ተጨማሪ ጥናታዊ ጽሑፎችና ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *