የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት ይካሄዳል
በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤት አገልግሎት ማስተባበሪያ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ የሚያካሂደውን የግቢ ጉባኤያት ሴሚናር ከየካቲት ፳፩-፳፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ በቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን (በብሔራዊ ሙዚየም) ያካሂዳል፡፡
በሴሚናሩ ላይ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት የሚከናወኑ ሲሆን ከአቀባበል ጀምሮ ትምህርተ ወንጌል፣ የማኅበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ለውጥ በግቢ ጉባኤያት ፣ የግቢ ጉባኤያት ሁለንተናዊ አገልግሎት ተሚክሮ፣ የግቢ ጉባኤት አገልግሎት ትግበራ ተሞክሮ (በተመረጡ ማእከላት)፣ የቤተ ክርስቲን ፈተናዎችና የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት በተሰኙና በሌሎችም ዝግጅቶች ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡

በመርሐ ግብሩም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ከ፬፻፶ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙ ሲሆን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የግቢ ጉባኤያት የሥራ አስፈጻሚዎች፣ የስድስቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች፣ የማእከላትና የወረዳ ማእከላት የግቢ ጉባኤያት ዋና ክፍሎች ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ፡፡
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!