ማኅበረ ቅዱሳን የድጋፍ ማሰባሰቢያ የዕጣ ትኬት ማዘጋጀቱ ተገለጸ

ማኅበረ ቅዱሳን የተቋማዊ ለውጥ ትግበራን ተግባራዊ በማድረግ አገልግሎቱን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ይህን ተከትሎ በተከለሰው የግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት መሠረት በግቢ ጉባኤያት (በዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች) ለሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በሃይማኖት እና በሥነ ምግባር አንጾ ለማውጣት ለሚተገብራቸው የመምህራን ማፍራት፣ የመመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት፣ እንዲሁም የቨርቹዋል ሥልጠና ማእከል ማቋቋሚያ የሚውል የድጋፍ ማሰባበሰቢያ የዕጣ ትኬት አዘጋጅቷል፡፡ የዕጣ ትኬቱንም ከሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥርጭት እና ሽያጭ መጀመሩን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አበበ በዳዳ ገልጸዋል፡፡

የዕጣ ትኬቱም ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው፣ ለማኅበሩ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለሌሎች ደጋፊ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን የቀረበ ሲሆን የአንድ ትኬት ዕጣ ዋጋ 100 (አንድ መቶ ብር) ብር መሆኑን አቶ አበበ ገልጸዋል፡፡

የዕጣ ትኬቱም ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያካተተ ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡ ከሽልማቶቹ መካከል፡-

  • ለሰባት ቀናት ወደ ቅድስት ሀገር የኢየሩሳሌም ጉዞ (ጉብኝት)፣
  • ለሰባት ቀናት ወደ ግብጽ ገዳማት ጉዞ (ጉብኝት)፣
  • ለአምስት ቀናት ከአንድ ቤተሰብ ጋር (በአውሮፕላን) ከኢትዮጵያ ገዳማት ወደ አንዱ መንፈሳዊ ጉብኝት እና ሌሎችንም ልዩ ልዩ ዕጣዎችን አካትቷል፡፡

ትኬቱን ከግቢ ጉባኤ ተማሪዎች፣ ከማኅበረ ቅዱሳን አባላት እንዲሁም በማኅበሩ የልማት ተቋማት ሱቆች ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ዕጣው የሚወጣበት ቀን ኅዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ነው፡፡

ዘገባው፡- የማኅበረ ቅዱሳን ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ነው፡፡ 

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *