ማኅበረ ቅዱሳን በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስተምራቸውን የግቢ ጉባኤት ተማሪዎችን አሰመረቀ
ማኅበረ ቅዱሳን ላለፉት ዓመታት በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መደበኛ ትምህርታቸውን ሲከታተሉና በግቢ ጉባኤያት መንፈሳዊ ትምህርት በመማር ላይ ይገኙ የነበሩ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን ከሰኔ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከየማእከላቱ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በልዩ ልዩ መርሐ ግብራት በማስመረቅ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳንም ባሉት መዋቅሮቹ መሠረት ከየማእከላቱ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡- ጅግጂጋ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳንስና ቴክሎሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ወላታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ … ሌሎችም በማስመረቅና ለማስመረቅ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የደረሱን መረጃዎች ያለመክታሉ፡፡
በ2017 ዓ.ም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተመረቁት መካከል በየትምህርት ክፍሎቻቸውና ከየተቋማቱ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን በፎቶ ግራፍ አስደግፈን እናቀርባለን፡፡ ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ ይዘን እንመጣለን፡፡




Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!