• እንኳን በደኅና መጡ !

አንፀባራቂና የደስታ በዓል

እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር ፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር ፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ እልል ይበል፡፡ በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር ፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡

በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር ፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡