‹‹የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው:: እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል›› (ዘፍ. ፪:፲)

ከኤዶም  ፈልቀው ምድርን ከሚያጠጡት አራት ወንዞች ኤፌሶን፣ ጤግሮስ፣ ኤፍራጥስ፣ መካከል ሁለተኛው ግዮን ወይንም ዓባይ ወንዝ የሀገራችን ሲሳይ /በረከት/ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክሮች ናቸው፡፡ ‹‹ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤዶም ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለዐራት መዓዝን ይከፈል ነበር፡፡ የአንደኛው ወንዝ ስም ኤፌሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፡፡ የዚያችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፡፡ በዚያም የሚያብረቀርቅ ዕንቊ አለ፡፡ የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል፤ የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሶር ላይ የሚሄድ ነው፡፡ አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው›› እንዲል፡፡ (ዘፍ. ፪:፲-፲፬)

‹‹እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው›› (ዕብ. ፲፩፥፩)

ማንኛውም የሕይወት ውጣ ውረድ ቢያጋጥመን በእምነት ከጸናን የማናልፈው ነገር የለም፡፡ የማንዘለው የችግር እና የመከራ ግንብ፣ የማንሻገረው ባሕር እና መሰናክል አይኖርም፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር ከኖርን የሚያስፈራን አንዳች ነገር አለመኖሩን ሲያስረዳ ‹‹በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሔድ፤ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል›› ብሏል፡፡ (መዝ. ፳፪፥፬)

‹‹ድኀነት››

የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ያጣውን የተፈጥሮ ጸጋ ክብር በአዲስ ተፈጥሮ እንደገና ለመታደል መብቃቱን ለመግለጽ የሚነገር ልዑል ቃል ‹‹ድኀነት›› ነው፡፡ ድኀነት የሚለው ቃል አዳም በክርስቶስ የታደለውን የሕይወተ ሥጋና ሕይወት ነፍስ፣ በረከተ ሥጋና በረከተ ነፍስ ጸጋ ወይም በሌላ አነጋገር የሞተ ሥጋና የሞተ ነፍስ ድቀት የደረሰበት አዳም በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘው ትንሣኤውና ሕይወት የሚገለጽበት ሕያው ቃል ነው፡፡

‹‹የሱራፌል አምሳላቸው ቅዱስ ያሬድ››

እግዚአብሔር አምላክን ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ በመንበሩ ፊት ቆመው እንደሚያመሰግኑ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያለ በመላእክት ቋንቋ ፈጣሪውን በማመስገኑ እና ዜማውን ከእነርሱ በመማሩ በመጽሐፈ ስንክሳር ‹‹አምሳሊሆሙ ለሱራፌል፤ የሱራፌል አምሳላቸው›› ተብሏል፡፡

“ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ትንቢተ ዮናስ ፪፥፲)

እግዚአብሔር ከበሽታ ይፈውሳል፤ ከችግርና መከራም ይሰውራል፡፡ በየጸበል ቦታው ተጠምቀው ከኤች አይ ቪ፣ ከካንሰር እና ከሌሎች በሽታዎች የተፈወሱ ሰዎች እንዳሉ ዓይናችን እንዲሁም የሕክምና ማስረጃዎች ምስክሮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ኃያል አምላክ፤ ሥራውም ድንቅ ነው፤ ተአምራትንም ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ከእርሱ ለማግኘት እምነት ያስፈልጋል፡፡

“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ” (ትንቢተ ዮናስ ፪፥፫)

በመጀመሪያ ራሳችን “በደለኛው እኔ ነኝ፤ ኃጢአተኛ ነኝ፤” ብለን አምነን መጸጸት አለብን፤ ጸጸትም ወደ ንስሓ ይመራናል፡፡ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና ውስጣችንን ከክፋት ሳናነጻ በሐሰተኛ አንደበት በንጸልይና ምሕረትን ብንለመን ልመናችንን አይቀበለንም፤ ሁሌም እርሱን በመፍራት መኖር እንዳለብን ቃሉ ይገልጻል፤ “ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” (መጽሐፈ ምሳሌ ፳፫፥፲፯) እንደተባለው እግዚአብሔርን አምላክን በንጹሕ ልቡና ልንማጸን ይገባል፡፡

“የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” (ገላ. ፮፥፪)

የክርስቶስ ሕግ ፍጻሜ ፍቅር ነው። ፍቅር አንድ ሰው ከሌላው ጋር በየዕለቱ የሚያደርገው ግንኙነት፣ በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ልባዊ መዋደድና ጥልቅ መንፈሳዊ ጸጋ ነው። በሰዎች መካከል በሚኖረው መልካም ግንኙነት የተነሳ አንዱ ለሌላው የሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ ፍቅር ነው።

“ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” (ሉቃ.፩፥፵፰)

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምናመሰግናት ስለተሰጣት ጸጋ እና ክብር ነው። የተሰጣት ክብር ደግሞ ከጸጋ ባለቤት ከልዑል እግዚአብሔር መሆኑን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ስለ ተሰጣትም የእግዚአብሔር ጸጋ የሔዋን መርገም በእርሷ ላይ ተቋረጠ እንዲህ ያለ ስጦታ ለአዳም እና ለዘሩ እስከ ዘለዓለም ለሌላ አልተሰጠም።›› በዚህ ብቻ ሳይሆን ስለ ንጽሕኗዋ፣ ስለ ቅድስናዋ ጭምር ምስጋና እናቀርባለን ።

“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ቅዱስ ያሬድ)

በመጻሕፍት አምላካውያት (አሥራው መጻሕፍት) እና በሊቃውንት አበው አስተምህሮ የተነገሩ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናዋን ቅድስናዋን የሚመሰክሩ መውድሳት ቅኔያትና ዝማሬያት እንዲሁም በሰፊው የተገለጡትን ምስክርነቶች ስንመለከት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ የተገኙ እንዳልሆነ አስተዋይ ሰው በቅጥነተ ሕሊና ቢረዳው የሚያውቀው እውነት ነው፡፡

“ጽና፥ እጅግም በርታ” (መጽሐፈ ኢያሱ ፩፥፯)

እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅ አብዝቶ ሲበድል ሌላ ጊዜ ደግሞ የሰውን ልጅ ለበለጠ ዋጋ ማዘጋጀት ሲፈልግ መቅሰፍትን ወደ ምድር ይልካል፡፡ በበደል ምክንያት የሚመጣው መቅሠፍት አሁን ዓለምን እያስጨነቀ ያለው ኮሮና በሽታ አይነት ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሰዓት እኛም በክርስቶስ ክርስቲያን የሆንን የክርስቶስ ልጆች እንደመሆናችን መጠን በጾም በጸሎት ይህን የመከራ ጊዜ ልናንልፍ ይገባል፡፡