ቤተ ክርስቲያንና የፓትርያርክ ምርጫ
ነሐሴ 25 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊትና ሐዋርያዊት መሆኗን ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ይቀበላሉ፤ በመሠረተ እምነታቸው ውስጥም አካትተው በጸሎትና በአስተምህሮ ይጠቀሙበታል፡፡የዚህ መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ይህ ትምህርት ቢኖርም ነገር ግን መልእክቱን በአግባቡ ካለመረዳት የተነሣ እነ አርዮስና መቅዶንዮስ በትውፊት ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መሠረት መቀበልን ቸል ብለው በራሳቸው መንገድ ሔደው ስለሳቱ በጉባኤ ኒቅያ በማያሻማ መንገድ ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ቅድስት፣ ሐዋርያዊት እና ኩላዊት መሆኗን አስቀመጡ፡፡ በኋላ በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ደግሞ ሁላችንም እንድንጸልይበት በተዘጋጀው አንቀጸ ሃይማኖት ላይ (ጸሎተ ሃይማኖት) ‹‹ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት›› የሚለው የጸሎታችን መፈጸሚያ እንዲሆን ተደነገገ፡፡ በዚህም መሠረት እነዚህን ዓለም አቀፍ ጉባኤያት የሚቀበሉ ሁሉ የሚቀበሉትና የሚመሩበት መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት /doctrine/ ሆነ፡፡
ይሁን እንጂ እየዋለና እያደረ ሲሔድ ቃላቱን ተርጉመው የሚረዱበት ሁኔታ እንደገና እየተለያየ መጣ፡፡ ለምሳሌ ያህል ከዚሁ አንቀጸ ሃይማኖት የሚነሱትን ሦስት መሠረታዊ ልዩነቶች ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ራሱ‹‹ቤተ ክርስቲያን›› የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ መረዳት ላይ ያለው ልዩነት ነው፡፡ በፕሮቴስታንቱ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በአንድ ቦታ የተሰባበሰቡት ሰዎች ኅብረት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አለፍ የሚሉትም ቢሆን በምድር ያለውን የአማኞቻቸውን ኅብረት አንድ መንጋ እንዲሁም በሰማይ ያሉትን ደግሞ ሁለተኛ መንጋ አድርው በአንድ እረኛ ሁለት መንጋ ሀሳብ የሚያራምዱ እንደ ሆኑ የምዕራባውያን ጽሑፎች ያሳያሉ፡፡ በምሥራቃውን ትውፊት ወይም በኦርቶዶክስ ግን ‹ቤተ ክርስቲያን› ማለት በምድር ያሉት ምእመናንና ተጋድሏቸውን የፈጸሙ ቅዱሳን ኅብረት ወይም አንድነት ናት፡፡ “እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አእጹቂሃ..” “ሥሮቿ በምድር ቅርንጫፎቿም በሰማይ ያሉ” የሚለው የቅዱስ ያሬድ ትምህርትም ለዚህ ትልቅ አስረጂ ነው፡፡ በሰማይ ያሉት በዚህ በእንግድነት ከምንኖርበት ምድር ተጋድሏቸውን ፈጽመው ሀገራቸው ገብተው ሽልማታቸውን ተቀብለው በድል ዝማሬ ላይ ያሉ ሲሆን በዚህ ያለነው ደግሞ በዕድሜ ዘመናችን እየተጓዝን ያለንና ገና ተጋድሏችን ያለፈጸምን መሆናችን እሙን ነው፡፡ ሆኖም በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና ብልቶቹ በሆንለት በቤተ ክርስቲያን ራስ በክርስቶስ አንድ ስለሆንን ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብቻ ናት፤ መንጋው አንድ እረኛውም አንድ፡፡ ለምሳሌ በእኛም ሆነ በሌሎቹ ኦርቶዶክሶች ያለውን ቅዳሴ በአስተውሎት ብንመረምረው ይህን ዶግማ ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ ወደ ፊት በደንብ የምናየው ቢሆንም ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መነሻውና መሠረቱ ይህ ነው፡፡
ታዲያ ይህን ‹‹ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት›› የሚለውን አንቀጹ ራሱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆኑ ሁሉም ቢቀበሉትም በትርጉም ግን ልዩነት ተፈጥሯል፡፡ የሮማ ካቶሊክ ‹አንድነትን›› በሮማው ፓፓ ሥር በመተዳደር ስትተረጉመው ኦርቶዶክሶቹ ግን አንድነት የሚገለጸው ዓለም በሙሉ በአንድ በመተዳደሩ አይደለም፤በምድር ተጋድላቸውን እያደረጉ ያሉ ምእመናንን በአንድ ምድራዊ ሃይማኖታዊ ተቋም አስተዳደርም የአነድነቱ ምንጭ አይደለም፤ ነገር ግን አማናዊ ሥጋውንና ደሙን ስንቀበልና የክርስቶስ ብልቶች ስንሆን ያን ጊዜ በአንዱ በክርስቶስ አንድ እንሆናለን ግንዱ አንድ ስለሆነ በዚያ የወይን ግንድ ያሉ ምእመናን ሁሉ በዚያው ግንድ ላይ በመሆናቸው ወይም አካሉ በመሆናቸው አንድ ናቸው፤ቤተ ክርስቲያንንም አንድ የሚያሰኛት ይህ የአንዱ ክርስቶስ ብልትነታችንንና አንድ አካል መሆናችን ነው ፡፡ “…ይዌልጦሙ በቅጽበት አባላተ ክርስቶስ ይኩኑ፤ በኃይለ ጥበቡ መንክር ወዕጹብ ኪኑ” “ድንቅና ዕፁብ በሆነ በጥበቡ ኀይል የክርስቶስ አካላት ይሆኑ ዘንድ በቅጽበት ይለውጣቸዋል፡፡” እንዳለ የመልክአ ቁርባን ደራሲ፡፡የኦርቶዶክሳውያን ትርጓሜ ይህን መንፈሳዊነትንና ከክርስቶስ ጋር ያለንን ውሕደት መሠረት ያደረገ ነው፡፡
ከዚሁ ጋር በትልቁ መሠረት የሚሆነው ደግሞ ‹‹ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት›› የሚለው እምነት ነው፡፡ እዚህም ላይ ትልቅ ልዩነቶች አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርዊት ናት የምትባለው መቼ ነው የሚለውን ጥያቄ ሲመልሱ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስት ነገሮች ሲሟሉ ነው ይላሉ፡፡ የመጀመሪያው ሢመተ ጵጵስና ወፓትርያርክን የሚመለከት ነው፡፡ ይህም አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት የምትባለው ጌታ ከሾማቸው ከሐዋርያት አንሥቶ ያልተቋረጠ ክትትል ያለው የሢመት ሐረግ ሲኖር ነው፡፡ ለምሳሌ የእኛ ከቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ አንሥቶ ሳይቋረጥ እስከ ቄርሎስ ስድሰተኛ (116ኛው) ፓትርያርክ ከደረስ በኋላ ለእኛ 117ኛ ሆነው አባ ባስልዮስ ኢትዮጵያዊ ተሾሙ፡፡ አሁን 121ኛው አባ ጳውሎስ ሆኑ ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊት የሚያሰኘው ደግሞ ሐዋርያዊ ትዉፊትን ተቀብላ የምትተገብር መሆኗ ነው፡፡ ከእነዚህም አንዱ ጳጳሳትን በተለይም ፓትርያርኮችን የምትመርጥበት ሐዋርያዊ ትዉፊት ወሳኙ ነው፡፡ ሦስተኛው ቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ የሚያሰኛት ደግሞ ሐዋርያዊ ክትትሉን የጠበቀ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ነው፡፡ ዶግማ የሚባለውም የዚህ ትርጓሜ ውጤት ነው፡፡
ከእነዚህ ነጥቦች ተነሥተን የእኛን ቤተ ክርስቲያን ሂደት (Experiance) መዳሰስ ቅድሚያ የሚሰጠው ሆኖ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም አንደኛ በታሪካችን ውስጥ ከነበሩት ጠንካራ ጎኖች ብቻ ሳይሆን ከድከመቶቹም የምንወስዳቸውን ጥቅሞች በቅርበት ለመመርመር፤ ሁለተኛም ከዚያ ተነሥተን ወደፊት የምንሔድበትን ለማየት ስለሚጠቅም ነው፡፡
ቀደም ብለን እንደገለጽነው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት የምትባለው ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ሲመተ እድ ባለተቋረጠና ክትትል ባለው ሐዋርያዊ ክህነት (Apostolic succession)እስካሁን በመኖሯና ሐዋርያዊ ትውፊትንም ከዚያው ሳትወጣ የምትፈጽም በመሆኗ ነው፡፡ ሆኖም በታሪካችን ሐዋርያዊ ትውፊትና ቀኖና የተፈተኑበት ጊዜ አልነበረም ማለት አይደለም፡፡ ከሁለት ሺሕ ዓመት አገልግሎት አንጻር ሲታይ አጋጣሚዎች ጥቂትና ጊዜዎቹም አጫጭር ቢሆኑም ከትፊዉቱ የመውጣትና የውጤቱንም መከራና ፈተና ማጨድ እንደነበረ ግን ታሪካችን ያስረዳል፡፡ ምንም እንኳ ዘመኑ ትንሽ ዕድሎቹም ጥቂት የነበሩ ቢሆኑም ያስከተሉት ጥፋትና ጉድለት ግን ትንሽ አልነበረም፡፡ሆኖም በየዘመኑ የነበሩ አባቶች ከችግሮቹ እየተማሩ ትውፊታቸውን አጥብቆ ወደመጠበቅ በመመለስ ከችግራቸው ወጥተዋል፡፡ ለመሆኑ ቀኖናውና ትውፊቱ ምንድን ነው?
ትውፊቱ
የቤተ ክርስቲያንን የጵጵስናና የፕትርክና ሹመት ታሪክ ጸሐፊዎች መነሻ የሚያደርጉት ጌታችን ሐዋርያትን የመረጠበትን ሁኔታና በሐዋርያት ሥራ ላይ የተገለጸውን የማትያስን ምርጫ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ‹‹ ሐዋርያዊት›› በሚያሰኟት በእነዚህ ሁለት የምርጫ ክስተት ውስጥ ሦስት መሠረታዊ መስፈርቶችን እንደ ምሳሌ ይወስዳሉ፡፡ እነዚህም
1ኛ) የሐዋርያት ከተርታው ሰው ውስጥ መመረጣቸው
ታሪክ ጸሐፊዎቹ እንደሚሉት ሁሉን ማድረግ የሚቻለው ጌታ ከምሁራነ ኦሪት ቅኖቹን መምረጥና ማብቃት መለወጥ እየተቻለው እነርሱን ትቶ ከተርታ ሰዎች ምንም ካልተማሩትና ምንም ልምድም ሆነ ዕውቀት የሌላቸውን መርጦና አምጥቶ አስተምሮ ቅዱሳን ሐዋርያትን የሾመው ወደ ፊት ፓትርያርኮች ከአነሥተኛው መዓርግ እየተመረጡ እንዲሾሙ ሲያሰተምረን ነው ይላሉ፡፡ እንዲያውም እንደ ቅዱስ ጳውሎስና እንደ አጵሎስ ያሉትን ምሁራነ አሪት እንደሚመልሳቸው እያወቀና ክብራቸውንም በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ቁጥሩም መዓርጉም ከሐዋርያት ሆኖ ሳለ መጀመሪያ ያልተመረጠው ምርጫው መንፈሳዊነትን እንጂ ዕውቀትን መሠረት ያደረገ እንዳይሆን ሥርዓት ሲሠራልን ነው በማለት ያስረግጣሉ፡፡ ጌታ ሐዋርያትን ከመረጠ በኋላ ግን አስተምሯቸዋል፤ በዚህም መሠረት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በተገቢው መንገድ ለአገልግሎትና ለምሥጢራት በሚያስችል ሁኔታ ከተማረና በርግጥ መንፈሳዊ ሆኖ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጠብቆ ከተመረጠ ሌላውን ዕውቀት ከራሱ ከጌታ ሊያገኘው ይችላል ባዮች ናቸው፡፡
2ኛ)የሰዎች ድርሻ
በቅዱስ ማትያስ ምርጫ ሒደት ውስጥ ከተገኙት ሁለት መሠራታዊ ትውፊቶች አንዱ ደግሞ ሐዋርያት መጀመሪያ ሁለት ሰዎችን መርጠው ድርሻቸውን መወጣታቸው ነው፡፡ ስለዚህ አባቶችን በመምረጥ ሒደት ሓላፊነት ያለባቸው አካላት አሉ፡፡ እነዚህ አካላት ግን ልክ እንደ ሐዋርያት ሊሾም ከታሰበው በላይ ቁጥር ያላቸውን መርጠው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሐዋርያት አንድ ሰው በይሁዳ ለመተካት ሲፈልጉ ሁለት እንዳቀረቡት ሁሉ ለመጨረሻው አባትነት ለፓትርያርክም አባቶች መምረጥ ያለባቸው ከአንድ በላይ መሆን አለበት፡፡
3ኛ) የእግዚአብሔር ምርጫ
ቅዱሳን ሐዋርያት ማትያስንና በርናባስን (ዮሴፍን) ከመረጡ በኋላ ከሁለቱ አንዱን የመምረጡ ድርሻ ግን የእግዚአብሔር ነበረ፡፡ ስለዚህ ማንኛችንም ቢሆን ከሐዋርያት ልንበቃ አንችልምና በወደደው መንገድ የእግዚአብሔርን የመምረጥ ዕድል የሰጠ መሆን አለበት፡፡የጥንታዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትውፊትም በእነዚህ መሠረቶች ላይ የተገነባ የሰውንና የእግዚአብሔርን ድርሻ በግልጽ የሚያስቀምጥ ነበር ይላሉ፡፡
ቀኖናውስ?
‹‹የእግዚአብሔርን መንጋ በእውቀት ለመጠበቅ ፍጹም የሆነ የሰው እጥረት አለ፡፡… ትክክለኛ የቀኖና እውቀትም የለም፡፡ ኃጢአትን ለመሥራት ሙሉ ነጻነት አለ፡፡ ሰዎች በአማላጅ ክህነትና እልቅና በተሾሙ ጊዜ ውልታቸውን ለመመለስ ሲሉ ቀኖናዊ ጥፋቶችን ቸለል ይላሉ፡፡›› ባስልዮስ ዘቂሳርያ /Basil of Caesaria, To the Italians and Gauls, letter 92/
“አንድ ጳጳስ በድርቅና በረሃብ፣ በተሾመባት ከተማ ትንሽ መሆን፣ በሕዝቡ ማነስ፣ በቂ ገቢ በሀገረስብከቱ ባለመኖሩና በመሳሰሉት ምክንያት ከተሾመባት ከተማ ወይም መንደር ተነሥቶ ወደ ሌላ አይሂድ፤ ከዚህ የተሻለ ይሰጠኝ ብሎም አይጠይቅ፤ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር የሚከፈለው ዋጋ አለውና” ይላል፡፡ በዚህ መሠረት
1ኛ) አንድ (ሊቀ) ጳጳስ ወደ ፕትርክና ቢመጣ እንደሚስት የምትቆጠርለትን ሀገረ ስብከቱን በማቅለሉና ሌላ የተሻለች መንበር (ሚስት) በመፈለጉ ምክንያት ብቻ የተነቀፈ ነው፡፡
2ኛ) ለፕትርክና ሲሾምም ጳጳሳቱ እጃቸውን የሚጭኑበት ‹‹ በ…ሀገር እና…ከተማ›› ብለው ስለሆነ ሁለተኛ እንደ ማግባት ተቆጥሮ እንደ ዝሙት ያስቀጣዋል ወይንም ክህነቱን ያሳጣዋል ይላሉ፡፡
3ኛ) ጌታ እንዳደረገው ወደ ላይኛው ሥልጣን የሚመጡት ከታችኛው ከአበ ምኔትነትና በታች ካለው እንደሆነ ትውፊቱ ያስገድዳልና፡፡
ይህንን ሀሳብ በትክክል ለመረዳት ግን የፓትርያርክን መሠረተ ሀሳብ በደንብ መፈተሽና በትክክለኛው ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በሐዋርያት ትውፊት መሠረት ፓትርያርክ ወይንም ፖፕ የሚለው ቃል ራሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው ከ232-247 ዓ.ም. ድረስ በእስክንድርያ መንበር በተሾመው በአባ ሔራክልዮስ ዘመን ነው፡፡ ይህም ማለት ፓትርያርክነት በክህነት መዓርግ ብልጫ የለውም ማለት ነው፡፡ ልክ በዲያቆንና በሊቀ ዲያቆን ወይም በጳጳስና በሊቀ ጳጳስ ወይም ደግሞ በቄስና በቆሞስ መካከል የሥልጣነ ክህነት ልዩነት እንደሌለው ሁሉ በጳጳስና በፓትርያርክም መካከል የሥልጣነ ክህነት መበላለጥ የለም፡፡ ይህም ማለት ዲያቆንን ሊቀ ዲያቆን በማድረግ ሒደት ድጋሚ የዲቁና ሥልጣን እንደማይሰጠው ሁሉ ወይም ድጋሚ ክህነት ቢሰጠው ውግዘት ያለበት እንደሆነው ሁሉ በፕትርክና ጊዜም የሚሰጠው ክህነት የጵጵስና ከሆነ ድጋሜ ክህነት ተሰጠው ስለሚያሰኝና በሁለተኛ ሀገረ ስብከትም ተሾመ የሚለውን ትርጉም የሚያመጣው ምሥጢር ይህ ስለሆነ ነው ጳጳስ ሀገረ ስብከቱን ትቶ ፓትርያርክ እንዳይሆን ቀኖናው የሚከለክለው፡፡ ይህ ከሆነ ፓትርያርክ ማለት የትክክል የበላይ ( Father among equals) ነው እንጂ የጳጳሳት ሁሉ ፍጹም የበላይ( father above equals) አይደለም፡፡ እንግዲህ ግብጾች እየጠበቁት ነው የሚባለው ይህ ነው፡፡
ሙሉውን እዚህ በመጫን ያንብቡ


ጻድቃንን ማሰብ ሥራቸውን መዘከር ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን ያጐለምሳል፡፡ የበረከታቸው ተሳታፊ በማድረግ በነፍስ በሥጋ የሚታደገንን የሚረባን፤ የሚጠቅመን ይሆናል፡፡ ስለጻድቁ አባታችን ስለ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም የምናስበው ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ በመንፈሳዊ አርአያነታቸው፣ በጸሎታቸውና በትምህርታቸው ከከበቡን የነፍስ ጠላቶች፤ ከርኲሳን መናፍስትና ከጨለማው ልጆች፣ ከክፉ ሰዎች ሽንገላና ተንኰል ለመሰወርና ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተቀበሉት ሥልጣን ምን ጊዜም ይሠራል፡፡ በጻድቃን መኖር ሀገር ከጥፋት ትድናለች፡፡ የጻድቃንን ስም ጠርቶ እግዚአብሔርን በመለመን በረከትና ረድኤት ይገኛል፡፡ ስለጻድቃን ብሎ እግዚአብሔርም ምሕረቱን ያድላል፡፡ ስለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቃንን እንድናስባቸው፣ በስማቸውም ለድሆችና ለጦም አዳሮች እንድንመጸውት መታሰቢያቸውን እንድናደርግ የምትመክረን፤ የምታስተምረን፡ ጻድቁ ተክለ ሃይማኖትንም የምናስባቸው ከዚሁ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በመነሣት ነው፡፡ ማቴ.10፥41-42 ጻድቃንን በሕይወተ ሥጋ ሳሉም ቢሆን፤ ከሞቱም በኋላ በአጸደ ነፍስ በጸሎታቸው ለሚታመኑ፣ በቃል ኪዳናቸው ለሚማጸኑ፣ የድኅነተ ሥጋ፣ የድኅነት ነፍስ ምክንያት ናቸው፡፡
በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው በገድል በትሩፋት መንፈሳዊ ተጋድሎአቸውን ቀጠሉ፡፡ ከደብረ ዳሞ ገዳም ወደሌላ ለመሄድ ሲነሡ፤ ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት አበምኔቱና መነኰሳቱ ሲሸኟቸው ሳለ፤ አርባ ክንድ ርዝመት ባለው ገመድ ገደሉን ለመውረድ እንደጀመሩ፤ ገመዱ ከካስማው ሥራ በመቆረጡ እንዳይወድቁ በተሰጣቸው ስድስት የብርሃን ክንፎች እየበረሩ፤ ክንፎቻቸውን እያማቱ ሦስት ምዕራፍ ሄደው ዐርፈዋል፡፡ ከዚያም ወደ ገዳመ ዋሊ ገብተዋል፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት “ለደካማ ኀይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለው ብርታትን ይጨምራል፡፡ ብላቴኖች ይደክማሉ፤ ይታክቱማል፡፡ ጐበዛዝትም ፈጽመው ይወድቃሉ፡፡ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠብቁ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስርም በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፡፡ “ኢሳይያስ 40፥29-31 ያለው ቃል በጻድቁ በቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሕይወት ሊተረጐም ችሏል፡፡ ከ1266-1267 ዓ.ም. አንድ ዓመት ሙሉ ገዳማተ ትግራይን በመጐብኘት ኢየሩሳሌምንና ግብፅ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ሲጎበኙ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አንድ ወር ሙሉ “ዳዳ” በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን 75 ክንድ ዘንዶ በጸሎት ኀይል በተአምራት ገድለውታል፡፡ አርባዓቱ እንስሳ /በኪሩቤልና በሱራፌል/ ስም ቤተ ክርስቲያን አንፀው፤ ታቦተ ሕግ /ጽላተ ሕግ/ አስገብተዋል፡፡ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ፤ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን መልሰው፤ አጥምቀው አቊርበዋል፡፡ በዚህም ተግባራቸው መድኀኒታችን “እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኀይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጎዳችሁም ምንም የለም” ሉቃስ 10፥19 ያለው ቃል ተፈጽሞላቸዋል፡፡ ክቡር ዳዊት በመዝሙር 90፥13-14 “በተኲላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውና ዘንዶውን ትረግጣለህ፡፡ በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም ዐውቋልና እጋርደዋለሁ፡፡” የተባለው ትንቢት ተፈጽሞላቸዋል፡፡ ከ1267-1289 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት፤ ስምንት ጦሮችን /ሁለቱን በፊት፣ ሁለቱን በኋላ ሁለቱን በቀኝ፣ ሁለቱን በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከቊመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን ስባረ ዐፅም አክብረው በሥርዓት አኑረውታል፡፡ እግራቸው እስኪሰበር የቆዩባቸው ዓመታት በቊጥር ሃያ ሁለት ናቸው፡፡ በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቊመት በተጋድሎ ብዛት፤ አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር፤ ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር፡፡
የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡ ከዚህ በኋላ ሄዶ፤ “የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ?” አላቸው “ሥጋዋን አግኝተን ቀበርናት” አሉት፡፡ እርሱም “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይህ ነገር አይመስለኝም” አላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ እንጂ ልማድህ ነው፡፡ አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም፤ አንተ እየተጠራጠርህ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ” አለው፡፡ እርሱም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሂዶ መቃብሩን ቢከፍተው የእመቤታችን ሥጋዋን አጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ደንግጦ ቆመ፡፡ ይህን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች” አላቸው፡፡ የያዘውንም ሰበን እያሳያቸው፡- “ቅዱስ ሥጋዋን የገነዛችሁበት ጨርቅ /ሰበን/ ይህ አይደለምን” ብሎ ሰበኑን ሰጣቸው፡፡ ይህንንም ለበረከት ተካፍለውታል፡፡ ከዚህ በኋላ በዓመቱ “ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ በማለት ጾም ጀመሩ፡፡ በ16ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ራሱ ቀድሶ አቁርቦአቸዋል፡፡
ቦታ ተሰይሟል፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓትና የሕግ መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገሥት በ15ኛው አንቀጹ መግቢያ ላይ “ጾምስ በሕግ ውስጥ በታወቀው ጊዜ የሰው ከምግብ መከልከል ነው፡፡ በደሉን ለማስተሥረይ ዋጋውን ለማብዛት እርሱን ወዶ ሕጉን ለሠራለት እየተታዘዘ የፈቲዉን ኀይል ያደክምበት ዘንድ ለነባቢትም ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ፤” በማለት የጾምን ምንነትና ጥቅም አጠር አድርጎ ያብራራል፡፡