ዕርገት
አምላካችን እግዚአብሔር ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላና በሁሉም ቦታ የሚኖር) በመሆኑ በባሕርይው መውጣት መውረድ የለበትም::‹ወረደ፣ ተወለደ› ሲባል ፍጽም ሰው መሆኑን የትሕትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም ከሰማያዊዉ ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም::በምድር ላይ ሊሠራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ::ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን የተለየበት ጊዜ የለም።ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋው የተደረገውን ዕርገቱን ያመለክታል።ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋው በምድር የስበት ቁጥጥር የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነዉ።አምላካዊ ሥልጣኑንም ያሳያል።