‹‹የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል›› (ዮሐ.፲፮፥፲፫)

ይህች ዓለም ከእውነት የራቀች መኖሪያዋን በሐሰት መንደር ያደረገች መሆኗ ይታወቃል፡፡ ሰው ማንነቱን አጥቶ በበደል ምክንያት በሐሰት ኖሯል፡፡ ሰው በፈቃዱ ጥፋት ምክንያት ከሚፈጽማቸው በደሎች ትልቁ በደል ውሸት ነው፡፡ ውሸት ተሸንፎ ይወድቃል፤ ከሕይወት ይርቃል፡፡ የኀጣአን ሁሉ ራስ ሐሰት ናት፡፡ ክፋትን ከራሱ አንቅቶ የበደለ ዲያብሎስ አቡሃ ለሐሰት፤ የሐሰት አባት የተባለው ለዚህ ነው (ዮሐ.፰፥፵፬)፡፡

ታቦተ ጽዮን

ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰላለች፤ ይህን ለመረዳት ስለ ታቦተ ጽዮን አሠራርና መንፈሳዊ ትርጉም አስቀድመን ልናውቅ ይገባናል፡፡

ጾመ ነቢያት

ጾመ ነቢያት ምንም እንኳን ዓላማው አንድ ቢሆንም የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ በዋነኝነት ነቢያት ስለጌታ ሰው መሆንና ስለ ሰው መዳን የጸለዩትን ጸሎት የጾሙትን ጾም በማሰብ፤ የአምላክ ሰው መሆንን ምሥጢር በትንቢት ተመልክተው ለእኛ ለሰው ልጆች የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ አስበው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡

‹‹መልአኩን ልኮ ያድነናል››

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስንዱ እመቤት ስለሆነች ይህ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል በወቅቱ ለእስራኤል ዘሥጋ መሆኑን በኅዳር ዐሥራ ሁለት ቀን ትመሰክራለች፡፡ በዚህ ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከግብፅ ምድር ከፈርዖን ግዛት ማውጣቱን ትዘክራለች፡፡

እውነተኛዋን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እናስጠብቅ!

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን በየዘመናቱ በሚነሱ መናፍቃን ስትፈተን እንደኖረች በታሪክ የታወቀ ነው፡፡ ዛሬም የተለያዩ የጥፋት ኃይሎች ቤተ ክርስቲያንንና ክርስትናን ለማጥፋት ያቀዱትን ትልም ለማሳካት በተዘዋዋሪና በይፋ ግፍ እና በደል እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡

‹‹እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሓ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል›› (ሐዋ.፲፯፥፴)

ለጊዜው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ስብከት የሰበከው አሕዛብ ለነበሩ የአቴና ሰዎች ቢሆንም፤ ለእኛም ጭምር ትልቅ መልእክትን የያዘ ቃል ነው፡፡ በተለይም ‹‹እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሓ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤››…..

ቅዱሱን መስቀል ቀብሮ ማስቀረት ቤተ ክርስቲያንንም ማዳከም አይቻልም

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉ ሰዎች ዘንድ ስንፍና ነውና፤ ለምንድነው ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው›› በማለት የተናገረው መስቀል እና ቤተ ክርስቲያን ለሚያምኑ ሰዎች ተጋድሎው የክብር መገለጫ ሲሆን ለማያምኑት ግን ሞኝነት መስሎ ስለሚታያቸው ነው።

‹‹የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው›› (መዝ. ፵፭፥፯)

ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔር በረድኤት ከሕዝቡ ጋር እንደሆነ፤ በፍጻሜው ሰው ሆኖ ከእኛ ጋር እንደሚሆን ሲናገር ‹‹የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው›› አለ፡፡

‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ›› (ዮሐ.፲፬፥፮)

በወልድ ውሉድ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ክርስቲያኖች ከተጠመቅንበት ጊዜ አንሥቶ የምንጓዝበት የድኅነት መንገድ መድኀነ ዓለም ነው፡፡

‹‹ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃሜውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ

ኃጢአት የኀሊናና የመንፈስ ሞት ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ‹‹የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው››…..