ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ የሚጠራውን ቡድን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አገደ
ነሐሴ 9 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን አብርሃም አንዳርጌ
በጠቅላይ ቤተ ክህነት አካባቢ ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ የሰየመውን ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የእገዳ ደብዳቤ ጣለበት፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የጉባኤው ዓላማና ፍላጎት ምን እንደሆነ እንደማይታወቅና እንዲህ ዓይነቱ ጉባኤ በቅዱስ ሲኖደስ ካለመቋቋሙም በላይ እውቅና ሳያገኝና ሳይፈቀድለት በራሱ ተነሳሽነት የሚንቀሳቀስ በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትም የማያውቀውና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዋና ጸሓፊና የከፋ ሸካ ቤንች እና ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፊርማ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በቁጥር 486/836/2004 ሐምሌ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. በተጻፈው ደብዳቤ መታገዱ ተገልጿል፡፡
“ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” በማለት ስለ ተቋቋመው ቡድን ያነጋገርናቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነት አንዳንድ የመምሪያ ሓላፊዎች ቡድኑ በምን ምክንያት እንደተቋቋመና ለምንስ በኅቡዕ መንቀሳቀስ እንደፈለገ እንዳልተረዱ ጠቅሰው ጉዳዩን ለቤተ ክርስቲያኗ ደኅንነት ሲባል በአንክሮ እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረው በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ሆነው የዚህን ሕገ ወጥ ቡድን አባላት በሆኑ ግለሰቦች ላይ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ርምጃዎች በቀጣይ እንደሚወስድም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡
ጉባኤውን እያደራጁ የሚገኙ ግለሰቦች አብዛኛዎቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት እያጡ የመጡ ግለሰቦች እንደሆኑ የሚናገሩት የቤተ ክህነቱ ምንጮች ቅዱስ ሲኖዶስ እነዚህ ግለሰቦች ሊፈጥሩት ካሰቡት ከፍተኛ አደጋ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊታደጋት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
የዚህ የእገዳ ደብዳቤ ግልባጭ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለሃይማኖትና ሥነ ሥርዐት ዳይሬክቶሬት ጀኔራል፣ ለብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት፣ እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ ኮምሽን እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ግልባጭ የተደረገ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡




የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም በነሐሴ ወር የሚደረገውን የማኅበሩን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክተው እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ያከናወናቸው የ20 ዓመት ጉዞዎች በጠቅላላ ጉባኤው ላይ አንሥቶ እንደሚገመግም ገልጸዋል፡፡
ያደረገው በ2004 ዓ.ም. መሪ እቅዱ መሠረት መሆኑን የጠቀሱት የክፍሉ ሓላፊ ወይዘሪት መቅደስ ዓለሙ፤ “ይህንን ለማቀድ ምክንያት የሆነን አባቶቻችን ከሰፊ የአገልግሎት ዘመናቸው በኋላ የሚታሰብላቸው የጡረታ አበል አለመኖሩ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ አባቶችም በቅርብ የሚረዳቸውና የሚንከባከባቸው ሰው የሌላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳልሰጡ በቂ ትኩረት ተነፍጓቸውና ተረስተው በየመቃብር ቤቱና ንጽሕና በተጓደለባቸው ሥፍራዎች ወድቀው የሚገኙትን አባቶች፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ባካሄድነው ጥናትና ባገኘነው መረጃ መሠረት መርጠን ረድተናል፡፡” በማለት ምክንያቱን አስረድተዋል፡፡
ምእመን ቤት ተጠግተው ለሚኖሩ አንድ አባት ሙሉ የሕክምና ወጪ በመሸፈን እንዲታከሙ አድርጓአል፡፡
በሦስት ሔክታር መሬት ላይ ጤፍ ለመዝራት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ያወሱት የአገልግሎት ክፍሉ ኃላፊ ወይዘሪት መቅደስ “መሬቱን በትራክተር ከታረሰበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሦስት ተከታታይ ጊዜያት የአከባቢው ገበሬዎች አርባ ጥማድ በሬዎቹን ይዘው እንዲሁም፤ ምእመናን በገንዘባቸውና በጉልበታቸው አማካኝነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ … ከደብሩ አስተዳደር ጀምሮ ሌሎችም መደበኛ አገልጋዮችና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት በጋራ እንሥራ የሚለውን መርሕ የተቀበሉ ናቸው፡፡ ይህም በሌሎች ቦታዎች ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አካላት መልካም ተሞክሮ ነው፡፡” በማለት በማጠቃለያ መልእክታቸው በፕሮጀክቱ ትግበራ ላይ የተባበሩትን ሁሉ አመስግነዋል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ያዘጋጀው መርሐ ግብር ከሐምሌ 12 እስከ ሐምሌ 15 ቀን ተካሄደ፡፡ ዝግጅቱ በሁለት ዐበይት ክፍሎች ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን፡- ይህም ከመክፈቻው ሐምሌ 12-14 በዐውደ ርዕይ፣ እንዲሁም ሐምሌ 15 ቀን 12 ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት መንፈሳዊ መርሐ ግብር የቀረበበት መሆኑ ታውቋል፡፡
“ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከዚህ ቀደም የተለያዩ ዐውደ ርዕዮችን ያዘጋጀ ሲሆን ሕፃናትን በተመለከተ ግን ይህ ዐውደ ርዕይ የመጀመሪያው ነው፡፡ ሕፃናትን የተመለከተ ዐውደ ርዕይ እንድናቀርብ የተፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ተገቢውን ትኩረት ለሕፃናት እንዲሰጥ ለመቀስቀስ ነው፡፡” በማለት ዐውደ ርዕዩ በሕፃናት ዙሪያ እንዲከናወን ምክንያት ስለሆነው ሁኔታ ያስረዳው ወጣት ዮሐንስ መረቀኝ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ምክትል ሰብሳቢ ነው፡፡

ምእመናን ተጠቃሚ በሚሆኑበት ሁኔታ ላይም ተወያይቶ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለተፈጻሚነታቸው በማእከሉ ስር ላለው ቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል ከባድ ኃላፊነት ሰጥቷል። የጉባኤውን ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሌላው አጀንዳ “የአውሮፓ ማእከል አባላት የአገልግሎት ሱታፌ ከማኀበረ ቅዱሳን ተልእኮ አንጻር” በሚል ርእስ የቀረበው ጥናት ነበር። በማእከሉ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ በተቋቋመው ቡድን ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ጥናት በሁሉም የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ አባላት በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር ታቅፈው በመስጠት ላይ ያሉትን አገልግሎት የዳሰሰ፣ ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን ነቅሶ ያወጣ፣ ወደፊት ሊደረግ የሚገባውን ያመላከተ ሰፊ ጥናት ነበር። ጉባኤው በጥናቱ ላይ ሰፊና ሞቅ ያለ ውይይት አድርጎ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በመጨረሻም ጉባኤው በቀረበለት የቀጣዩ የ2005 ዓ.ም. የአገልግሎት ዘመን ዕቅድ ላይ ተወያይቶ የማሻሻያ ዐሳቦችን በመስጠት ካጸደቀ በኋላ ማእከሉን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሚመራ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ መርጦ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል። ማእከሉ ስምንት የግንኙነት ጣቢያዎች እና አምስት ቀጠና ማእከላት ያሉት ሲሆን በስዊድን ቀጠና ማእከል የተዘጋጀው የዘንድሮው ጉባኤ የተሳካ እንደነበር የጉባኤው ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ቀጠና ማእከሉ ለጉባኤው መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉትን አባላትና ምእመናን እንዲሁም ተቋማት በተለይ ጉባኤው በተመቼ ሁኔታ ይካሄድ ዘንድ መሰብሰቢያ አዳራሽና የተሳታፊዎችን ማረፊያ ቤት ከሙሉ አገልግሎት ጋር በነጻ የሰጠውን በብሬድንግ የስዊድን ቤተ ክርስቲያን አመስግኗል።
