• እንኳን በደኅና መጡ !

በዓለ ጰራቅሊጦስ

በዲ/ን ዘአማኑኤል አንተነህ በዓለ ጰራቅሊጦስ ከዘጠኙ የጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው። ጰራቅሊጦስ ማለት ከአብ እና ከወልድ ጋር ለምንሰግድለት የዘለዓለም አምላክ ለሆነው ለሚያነጻ፣ ሊሚያጽናና እና ለሚቀድስ ለመንፈስ ቅዱስ የመጠሪያ ስም ነው፡፡ በዚህም በዓለ መንፈስ ቅዱስ ለማለት በዓለ ጰራቅሊጦስ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ይህ ታላቅ በዓል የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበት […]

በእንተ ዕርገት

መምህር በትረማርያም አበባው ዕርገት ዐርገ ዐረገ፣ ወጣ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ወደ ላይ መውጣት ማለት ነው፡፡ “ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ” (መሳ.፲፫፥፳) ከዚህ እንደምናየው ዐረገ ማለት ወደ ላይ ወጣ ማለት ነው፡፡ ይህ ቃላዊ ትርጓሜው ሲሆን ምሥጢራዊው ትርጓሜ ግን ዕርገት ማለት የሰው አምላክ መሆን ተብሎ […]

ዳግም ትንሣኤ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በኋላ የሚውለውን እሑድ ዳግም ትንሣኤ ብላ ሰይማ ታከብረዋለች፡፡ ይህም በአከባበር፥ በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡ ከትንሣኤ ዋዜማ ጀምሮ የሚጸለየው ጸሎት፣ የሚነገረው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤ በሙሉ በዚህ ቀንም ይደገማል፡፡ ዕለቱንም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ለሁለተኛ ጊዜ መታየቱን(መገለጡን) በማሰብ ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡ የሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡- […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን