• እንኳን በደኅና መጡ !

ከጎፋና ባስኬቶ ሀገረ ስብከት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም የሣውላ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የነበሩት በቀን 14 /5 / 2015 ዓ.ም በአቡነ ሳዊሮስ ከተሰጠው “የጳጳሳት ሹመት” ውስጥ ቆሞስ አባ ገ/መድኅን ገብረማርያም የጎፋና ባስኬቶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ተብለው የተሾሙትን ኮሚቴውና ሕዝቡ የማያውቀው ምንም አይነት ከጥያቄያችን ጋር ግንኙነት የሌለው ስለሆነ ኮሚቴውና ሕዝቡ በአሁኑ ሰዓት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በትዕግሥት መጠበቅ እንደሚገባ እና […]

ከጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በአሁኑ ወቅት ኤጲስ ቆጶሳትን ሾምን፤ በሚያገለግሉበትም ቦታ መደብን የሚሉ ሕገ ወጥ አካላት የሕግና የሥርዓት ምንጭ የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክብር የሚያቃልል፤ አንድነቷን የሚከፋፍል፤ ቀኖናዋንና ትውፊቷን የሚሸረሽር ተግባር ፈጽመዋል፡፡ የጉራጌ ሶዶ ሀ/ስብከት ጳጳስና የምሁር ኢየሱስ ገዳም የበላይ ጠባቂ ጳጳስ ተደርገው ሁለት ሰዎች ለጉራጌ ሀ/ስብከት መመደባቸውንም በአግራሞት ተመልክተናል፡፡ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን የማታውቃቸው ሕገ ወጥ ሿሚና […]

“የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ሃይማኖታዊ ክህደት፣ ቀኖናዊ ጥሰት እና አስተዳደራዊ ግድፈት የታየበትን የወሊሶውን “ሹመት” አወገዘ፡፡” የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ

የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ዛሬ ጥር ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት በአካሔደው አስቸኳይ ጉባኤ ሃይማኖታዊ ክህደት፣ ቀኖናዊ ጥሰት እና አስተዳደራዊ ግድፈት የታየበትን የወሊሶውን “ሹመት” ማውገዙ ተገለጸ፡፡ ጉባኤው በቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ሁሉን አቀፍ ክህደት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን ክህደቱን የፈጸሙት አካላት […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን