• እንኳን በደኅና መጡ !

ደብረ ዘይት

በእንዳለ ደምስስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት ተብሎ ይጠራል፡፡ ደብረ ዘይት በኢየሩሳሌም የሚገኝና የወይራ ዛፍ በብዛት ያለበት ተራራ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ፣ የተራቡትን እየመገበ፣ ለሚሹት እየተገለጠ ውሎ ማታ ማታ ግን ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እየወጣ ይጸልይ ነበር፡፡ “ከዚያም በኋላ ሕዝቡን አሰናብቶ ሊጸልይ ብቻውን ወደ ተራራ […]

“ልትድ ትወዳለህን?”

በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ አንዲት መጠመቂያ ነበረች፡፡ ይህች መጠመቂያም በእብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ስትባል አምስት አርከኖች ነበሯት፡፡ በዚያም ዕውሮችና አንካሶች፣ ሰውነታቸው የሰለለ በርካታ ድውያን ተጠምቀው ይድኑ ዘንድ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ወንዙ ወርዶ ውኃውን እስኪያነዋውጠው ድረስ ይጠባበቁ ነበር፡፡ ውኃው በሚነዋወጥበት ጊዜም በመጀመሪያ ወርዶ የተጠመቀባት ካለበት ደዌ ሁሉ ይፈወስ ነበር፡፡ (ዮ.፭፥፩-፬) በዚህ ሥፍራ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል ድኅነትን […]

ምኵራብ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንትን ምኵራብ ብላ ትጠራዋለች። ምኵራብ ሰቀላ መሰል አዳራሽ፣ የአይሁድ የጸሎት ቤት ማለት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን አይሁድ በኢየሩሳሌም ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጽሙበት ቤተ መቅደስ ነበር፡፡ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን    በመውረር ቤተ መቅደሳቸውን አፍርሶ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን ካፈለሰ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚገኙባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ምኵራብ መሥራት እንደ ጀመሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትይገልጻል፡፡ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን