• እንኳን በደኅና መጡ !

ሰሙነ ሕማማት (ሰኞ)

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎቹ የዐቢይ ጾም ሳምንታት በተለየ ሁኔታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ ለመከራ ተላልፎ የተሰጠበትንና አዳምና ልጆቹን ያድን ዘንድ በዕለተ ዓርብ በፈቃዱ በመስቀል ላይ መሰቀሉን በመስበክ ሕማሙንና ስቃዩን እያሰበች በጾም፣ በጸሎትና በሐዘን ታከብረዋለች፡፡ ምንባባቱ፣ የዜማ ክፍሎቹ ሁሉ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም በደል ሳይገኝበት አይሁድ በምቀኝነት ተነሣስተው ያደረሱበትን ስቃይ፣ በመስቀል ላይ እርቃኑን […]

ሆሣዕና በአርያም

ሆሣዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሆሼዕናህ” የሚል ሲሆን ትርጉሙም “እባክህ አሁን አድን” ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ “አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡” (፻፲፯፥፳፭-፳፮) እንዲል፡፡ የሆሣዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም […]

ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን፤ ድል ማድረግ ወይም አሸናፊነት ማለት ነው፡፡ ኒቆዲሞስ ከፈሪሳዊውያን ወገን ነው፡፡ ፈሪሳውያን ሕግን የሚያጠብቁ፣ ሕዝብን የሚያስመርሩ፣ እነርሱ የማይፈጽሙትን ሕግ በሕዝብ ላይ የሚጭኑ፣ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ አባታችን አብርሃም እያሉ የሚመጻደቁ ነገር ግን የአባታቸው የአብርሃምን ሥራ ከማይሠሩት ወገን እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ ፈሪሳውን ከመመጻደቃቸውም የተነሣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከወግና ከልማድ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን