መጋቢት 16 ቀን 2012

ወቅታዊውን ኮሮና በሽታ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን መንበረ
ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ፡-

በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የሰው ልጆችን ሕይወት በሞት እየቀጠፈ ያለው ተላላፊ በሽታ ለአገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ መምጣቱ ታምኖበት ወረርሽኙ ለመቋቋም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደምንገኝ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባሉባት ሕዝባዊ ኃላፊነት የተነሳ ለዚሁ የመከላከል ሥራ ራሱን የቻለ የተስፋ ግብር ኃይል በመቋቋም ህብረተሰቡ ከበሽታው እንዲጠበቁ ለማድረግ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ቋሚ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ በጉዳዩ በሰፊው በመነጋገር በጊዜያዊነት መዘጋት በሚገባቸው የሥራ ክፍሎች ላይ የሚከተለውን ወስኗል፡፡

1. ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የተዘጉ መመሪያዎች

ሀ. የመንበረ ፓትርያርክ ቅርሳቅርስ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር

  • ጉብኝት
  • የንባብ አገልግሎት

2. በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር ከአዲስ አበባ እስከ አህጉረ ስብከት ያሉ

ሀ.መንፈሳዊ ዪኒቨርስቲዎች

ለ. መንፈሳዊ ኮሌጆች

ሐ. ስልጠና ያልጀመሩ የካህናት ማሰልጠኛዎች

መ. መዋዕለ ሕፃናት

ረ. የአብነት ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ የመማር ማስተማሩ ሥራ ቁሞ ደቀመዛሙርቱና ተማሪዎች በእየቤታቸው የተማሩትን እየቀጠሉና እያጠኑ እንዲቆዩ፡-

3. በከፊል እንዲዘጉ የተደረጉ፡-

ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት እስከ መላው አህጉረ ስብከት ጽሕፈት ቤቶች ለአስቸኳይ ሥራ ከሚፈልጉና ተለይተው እንዲቆዩ ከሚደረጉ ሠራተኞች በስተቀር መላው ሠራተኞች በየቤታቸው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ሲገልጉና ጥሪ ሲደረግላቸው ከሚመጡ በስተቀር በቤታው እንዲቆዩ፤

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝባችንን ለሕማም ሞት አገራችንን ከልዩ ልዩ መቅሰፍትና ደዌ ይጠብቅልን፡፡

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት

ዋና ሥራ አስኪያጅ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ