በማኅበረ ቅዱሳን የጥናት እና ምርምር ማእከል

 

ሦስተኛው  ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት ጉባኤ

በጥናታዊ ጉባኤው የሚቀርብ

የጽሑፍ አጠቃሎ ለመላክ የቀረበ ጥሪ

ዓላማ                                           

ይህ “ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥናት ጉባኤ” የተዘጋጀው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/  በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል አስተባባሪነት ሲሆን መሪ ቃሉም  “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እና የሀገር ግንባታ”  የሚል ነው። ጉባኤው የሚካሄደው መስከረም ፲፩ እና ፲፪ ቀን ፳፲፪ ዓ.ም. (መስከረም 11 እና 12 ቀን 2012  ዓ.ም.)  ሲሆን የሚካሄድበት ቦታም በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የስብሰባ አዳራሽ (አዲስ አበባ አምስት ኪሎ) ይሆናል።

ቁልፍ ተናጋሪዎች 

 አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሠረት፡- በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር፣ ካምፓላ/ ኡጋንዳ

ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፡- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር ፣አዲስ አበባ /ኢትዮጵያ

ፕሮፌሰር እንደሻው በቀለ፡- የጄነቲክስ ጥናት ፕሮፌሰር የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የጽሑፍ አጠቃሎ ማቅረቢያ

የጉባኤው አዘጋጆች የተለያየ ሙያ ያላቸው ምሁራንን ጥናታዊ ጽሑፍ እንዲያቀርቡ እና አጠቃሎአቸውንም ከ450 ቃላት ባልበለጠ አዘጋጅተው እንዲልኩ ይጋብዛሉ። በቀረበው የአጠቃሎ ጽሑፍ ብስለት እና ጥራት መሠረት ምርጫ ተደርጎ ያለፉት ርእሶች ይፋ ይሆናሉ። አቅራቢዎች ከሚልኩት የጽሑፍ አጠቃሎ በተጨማሪ ሙሉ ስማቸውን እና የሚሠሩበትን ወይም የሚያገለግሉበትን ተቋም ከ“ግለ-ታሪክ” ጋር የሚገኙበትን አድራሻ አካተው በአንድ ገጽ እንዲልኩ ይጠየቃሉ። የተመረጡት የጽሑፍ አጠቃ