በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

 

 1. የፕሮጀክቱ ርእስ፡- የስብከት ማእከል አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፡ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት በሌሉባቸው አካባቢዎች የማእከል የስብከት ማዕከል አዳራሽ በመገንባት ምእመናን ተሰባስበው ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩ ይደረጋል፤

 • የሐዋርያዊ አገልግሎት በሚፈጸምባቸው ጠረፋማና ገጠራማ አካባቢዎች አዳዲስ አማንያንን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ ትምህርተ ሃይማኖት የሚማሩበት፣ ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጽሙበት፣ የሚጸልዩበትና እርስ በእርስ የሚመካከሩበት፣ ወጣቶችና ሕጻናት በሰንበት ት/ቤት ታቅፈው ተከታታይ ትምህርት የሚማሩበት 60 (ስድሳ) የማዕከለ ስብከት ማእከላትን መገንባት ነው፡፡
 • ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ ወጪ
 • የአንድ ስብከት ማእከል አዳራሽ ግንባታ ወጪ፡-75,000 (ሰባ አምስት ሽህ)
 • ለ60 ስብከት ማእከል አዳራሽ ግንባታ 4,500,000 (አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ)

አሁን ምእመናን እየተማሩ የሚገኙበት በወደፊት ገጠርና ጠረፋማ አካባቢ ምእመናን ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩበት የሚሠራ የስብከት ማእከል

 1. ፕሮጀክቱ ርስ፡- በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያገለግሉና ስበከተ ወንጌልን ለማጠናከር ቀዳሚ ሚና የሚጫወቱ ደረጃ አንድ ሰባኪያነ ወንጌልን ማፍራት፣
 • የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፡ አዳዲስ ተጠማቂያን ባሉበት የገጠርና ጠረፋማ አካባቢ ስበከተ ወንጌልን ተደራሽነት ለማሳደግ በ5 (አምስት) ጠረፋማ ቦታዎች 500 (አምስት መቶ) በተለያዩ ቋንቋዎች  የሚያገለግሉና ስበከተ ወንጌልን በማጠናከር ኢ-ጥሙቃንን በማስተማር ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመመለስ የሥላሴ ልጅነት እንዲያገኙ ቀዳሚ ሚና የሚጫወቱ ሰባኪያነ ወንጌልን ማፍራት፣
 • ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ ወጪ
 • ለአንድ ሠልጣኝ አማካኝ ወጭ ለአንድ ወር 3000 (ሦስት ሽህ ብር)
 • አጠቃላይ ለ500 (አምስት መቶ) ሠልጣኞች የሚያስፈልግ ወጭ 500*3000=1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር)

 1. ፕሮጀክቱ ርስ፡- በተለያየ ቦታ ለሚኖሩ ምእመናን ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ጥያቄ በቀጥታ በስልክ ምላሽ በመስጠት ምእመናንን ለማጽናት የጠፉትን ለመመለስ ይረዳል
 • የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፡ ሃይማኖታዊ ጥያቂዎችን በስልክ ምላሽ በመስጠት የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ምእመናን ለሚጠይቁት ጥያቂ ምላሽ በመስጠት የተለያዩ የስብከት ዘዴዎችን በመጠቀም ምእመናንን ማጽናት፣ የጠፉት መመለስና አዳዲሶችን ማጥመቅ
 • ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ ወጪ
 • አጠቃላይ በ4 (አራት) ዓመት የ4 (አራት) መምህራን ደመወዝ ወንበር ጠረጴዛ ማዳመጫ የቤሮ ዝግጅትና ኔቶርክ ዝርጋታ ጨምሮ የሚያስፈልግ ወጭ 1,421,400 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ አንድ ሽህ አራት መቶ ብር)

ማጠቃለያ

 የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እኔ እላካለሁ በማለት የሐዋርያዊ አገልግሎትን የማስፋፋት ኃላፊነት የእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አካል ድርሻ በመሆኑ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን  በስሑታን ትምህርት ለተወሰዱትና ቃለ እግዚአብሔርን ናፍቀው በሜዳ ለሚቅበዘበዙት ወገኖቻችን እንደርስላቸው ዘንድ “ኑ የወንጌል ማኅበርተኛ እንሁን!” እያለ ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የባንክ ሒሳብ ቍጥር፡- 1000195489541

አቢሲኒያ ባንክ

የባንክ ሒሳብ ቍጥር፡- 15376481

አዋሽ ባንክ

የባንክ ሒሳብ ቍጥር፡- 01304024224400

ስልክ ቍጥር፡- +251-9-60-67-67-67

ኢ-ሜይል፡-evangelism.program@eotcmk.org