በማኀበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባባሪያ

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ነጻ የትምህርት

ዕድል ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ “አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርት መርሐ ግብር” በሚል የዘመናዊውን እና የአብነቱን ትምህርት በማቀናጀት ተተኪ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ለማፍራት የዘመናዊ፣ የአብነትና የነገረ መለኮት ነጻ የትምህርት ዕድል እየሠጠ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የዚህ መርሐ ግብር ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን፡፡

ሀ/ ከአብነት  ወደ  ዘመናዊ  መማር  ለሚፈልጉ   

 1. በዲግሪና ዲፕሎማ (ሌቭል 3ና በላይ) መርሐ ግብር ለሚማሩ
 • በአንድ የአብነት ትምህርት ያስመሰከረ ወይም በነገረ- መለኮት ትምህርት የተመረቀ ሆኖ ቢያንስ አንድ ዓመትና በላይ ያገለገለ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
 • ቢያንስ በአንድ የቤተክርስቲያን ትምህርት ያስመሰከሩና ወንበር ዘርግተው በማስተማር ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ለአብነት መምህራን)
 • በገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ለሰባክያነ ወንጌል)
 • በቤተክርስቲያን ከሚሠጡ ትምህርቶች ቢያንስ በአንድ የአብነት ትምህርት ዘርፍ ጠንቅቆ የተማረና አምስት ዓመትና በላይ አገልግሎት የሠጠ ሆኖ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
 • ሌሎች ማኅበሩ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉና የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ፣
 1. በመሠናዶ (11ኛ ና 12 ኛ ክፍል) መርሐ ግብር ለሚማሩ
 • ወንበር ዘርግተው በማስተማር ሁለት ዓመትና በላይ የሆናቸው ሆኖ ዘመናዊ ትምህርቱን በሚማሩበት ወቅት ጉባኤውን ዘርግተው ማስተማር የሚችሉ (ለአብነት መምህራን) ፣
 • በምስክር ትምህርት ቤት በመማር ላይ የሚገኙና አንድ ዓመት በትምህርት ቤቱ የቆዩ ሆነው የዘመናዊ ትምህርቱን በሚማሩበት ወቅት ጉባኤውን መማር የሚችሉ (ለምስክር ት/ቤት ተማሪዎች)፣
 • በመጋቢ ትምህርት ቤት በመማር ላይ የሚገኙና ሁለት ዓመት በትምህርት ቤቱ የቆዩ ሆነው የዘመናዊ ትምህርቱን በሚማሩበት ወቅት ጉባኤውን መማር የሚችሉ (ለመጋቢ ት/ቤት ተማሪዎች)፣
 • ከሚያስተምሩበት ወይም ከሚማሩበት አብነት ትምህርት ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • ሌሎች ማኅበሩ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉና የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ፣

ለ/ ከዘመናዊ ወደ አብነት ት/ቤቶች ገብተው መማር ለሚፈልጉ

 1. በምስክር የአብነት ትምህርት ቤት  ለሚማሩ
 • በመጋቢ ት/ቤቶች የሚሰጠውን ትምህርት በአግባቡ የተማረና በምስክር ት/ቤቶች በመማር ለማስመስከር ብቁ የሆነ፣
 • በዘመናዊ ትምህርት ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ/ዲፕሎማ (ሌቭል 3ና በላይ) ያለው፣
 • ማኅበሩ በሚመድበው የአብነት ት/ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆነ፣
 • ሌሎች ማኅበሩ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ማሟላት የሚችልና የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፍ፣
 1. በመጋቢ የአብነት ትምህርት ቤት ለሚማሩ
 • መሠረታዊ የአብነት ትምህርት ዕውቀት ያለው ቢያንስ ንባብና ዳዊት ፣ግብረ ድቁናና ሰዓታት ጠንቅቆ የተማረ
 • በዘመናዊ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ/ዲፕሎማ (ሌቭል 3ና በላይ) ያለው፣
 • አብነት ት/ቤት ካልተስፋፋባቸውና ማኅበሩ በሙሉ ድጋፍ ከሚያስተምራቸው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ተመርቆ የወጣ፣
 • ከሚያገለግልበት አጥቢያ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
 • አብነት ትምህርት ቤት ካልተስፋፋባቸውና ጠረፋማ ከሆኑ አካባቢዎች የመጣ፣
 • ሌሎች ማኅበሩ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ማሟላት የሚችልና የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፍ፣

ሐ/ የነገረ መለኮት ትምህርት ለሚማሩ

 1. ከጠረፋማና የአገልጋይ እጥረት ካለባቸው ቦታዎች ለሚመጡ
 • ጠረፋማና የአገልጋይ እጥረት ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ሆኖ ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉና ተገቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
 • ማኅበሩ በሙሉ ድጋፍ ከሚያስተምራቸው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ተመርቀው የወጡ ተማሪዎች፣
 • በገዳማት 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የቆዩ መነኮሳት ሆነው ከገዳሙ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው በመማር ላይ የሚገኙና አንድ ሴሚስተር በላይ የተማሩ ደቀ መዛሙርት፣
 • ቢያንስ የ10ኛ ክፍል ትምህርትን ያጠናቀቁ፣
 • እድሜያቸው ከ 40 ዓመት ያልበለጠ፣
 • ሌሎች ማኅበሩ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉና የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ፣
 1. ከአብነት ትምህርት ቤት ለሚመጡ
 • በአንድ የአብነት ትምህርት ያስመሰከረና ቢያንስ አንድ ዓመትና በላይ ያገለገለ፣
 • በገዳማት 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የቆዩ መነኮሳት ሆነው ከገዳሙ የማስረጃ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 • መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው በመማር ላይ የሚገኙና ከሁለት ሴሚስተር በላይ የተማሩ ደቀ መዛሙርት፣
 • ቢያንስ የ10ኛ ክፍል ትምህርትን ያጠናቀቁ፣
 • እድሜያቸው ከ 40 ዓመት ያልበለጠ፣
 • ሌሎች ማኅበሩ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉና የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ፣

የምዝገባ ቦታዎች ፡-

 1. በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በአካል ቀርቦ መመዝገብ ይቻላል፡፡
 2. በሁሉም የማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት ጽ/ቤቶች ዘወትር ከ11፡30-1፡30
 3. በየግቢ ጉባኤያት ባሉ የአብነት ትምህርት ክፍላት ወይም በኢሜይል አድራሻ፡gedamat.abnet@eotcmk.org

     ኦሪጅናልና ኮፒ ማስረጃዎችን በመያዝ መመዝገብ ይቻላል፡

የምዝገባ ጊዜ፡- ከኅዳር 1/2012 ዓ.ም እስከ ጥር 30/2012 ዓ.ም ድረስ

የምዝገባ ሰዓት ፡- ከሰኞ እስከ ዐርብ ከጠዋቱ 3፡00-ማታ 1፡00 ፣

                 ፡- ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 -6፡30

   ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቢሮ፡ 011-8684774፣ 011-1553625

ሞባይል09 13 70 50 13 / 09 91 73 40 66 / 09 63 01 01 01

በቅዱሳት መከናትና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ

የአብነት ት/ቤቶች ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ዋና ክፍል

   ታኀሣሥ 2012 ዓ.ም