ሥረይ ግሦች

ክፍል ሁለት

ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! የ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት የሦስተኛ ወር የኅዳር የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜያችን የሆነውን ትምህርት ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ታስታውሱ እንደሆነ ባለፈው ትምህርታችን ላይ በግእዝ ቋንቋ ከግሥ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ‹‹ሥረይ ግሥ›› በግሥ አርእስት ቀተለ ዘርዝረን ለማየት ሞክረናል፡፡

በመቀጠልም ደግሞ ሥረይ ግሦቹን በግሥ አርእስት በቀደሰ፣ በተንበለ፣ በባረከና በማህረከ ሥር መድበን ርባታቸውን እንደሚከተለው አቅርበናል። በጥሞና ተከታተሉን!

. በቀደሰ ሥር የሚመደቡና የርባታ አመል ያላቸው ሥረይ ግሦች

ሥረይ ግሥ ትርጉም ሰዋስዋዊ ሙያ
ለበወ አስተዋለ ኃላፊ አንቀጽ
ይሌቡ ያስተውላል ትንቢት አንቀጽ
ይለቡ ያስተውል ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይለቡ ያስተውል ትእዛዝ አንቀጽ
ለብዎ/ለብዎት ማስተዋል ንዑስ አንቀጽ
ለባዊ የሚያስተውል ሣልስ ቅጽል
ለባዊት የምታስተውል አንስታይ ቅጽል
ልባዌ አስተዋይ ጥሬ ዘር
ልቡና አስተውሎት ጥሬ ምዕላድ
መለብው የሚያስተውል ባዕድ ቅጽል
ለቢዎ   አስተውሎ ቦዝ አንቀጽ

ልብ በቁሙ

ሰብሐ አመሰገነ ኃላፊ አንቀጽ
ይሴብሕ ያመሰግናል ትእዛዝ አንቀጽ
ይሰብሕ ያመሰግን ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሰብሕ ያመስግን ትንቢት አንቀጽ
ሰብሖ/ሰብሖት ማመስገን ንዑስ አንቀጽ
ሰባሒ አመስጋኝ ሣልስ ቅጽል
ሰባሒት የምታመሰግን አንስታይ ቅጽል
ስብሕት የተመሰገነች ሳድስ አንስታይ ቅጽል
ስባሔ ምስጋና ጥሬ ዘር
ሰቢሖ አመስግኖ ቦዝ አንቀጽ
ስብሐት ምስጋና ምዕላድ ዘር

ትውክልት፤ እምነት

ተወከለ ታመነ ኃላፊ አንቀጽ
ይትዌከል ይታመናል ትንቢት አንቀጽ
ይትወከል ይታመን ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይትወከል ይታመን ትንቢት አንቀጽ
ተወክሎ/ተወክሎት መታመን ንዑስ አንቀጽ
ውኩል   የሚታመን ሣልስ ቅጽል
ተወኪሎ ታምኖ ቦዝ አንቀጽ

 ኅሊና፣ ሐሳብ

ኀለየ አሰበ ኃላፊ አንቀጽ
ይኄሊ ያስባል ትንቢት አንቀጽ
የኀሊ ያስብ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
የሐሊ ያስብ ትእዛዝ አንቀጽ
ኀልዮ/ኀልዮት ማሰብ ንዑስ አንቀጽ
ኀላዩ አሳቢ ሣልስ ቅጽል
ኅሉይ የታሰበ ሳድስ ቅጽል
ኀልዮ አስቦ ቦዝ አንቀጽ
አንነገለገ ተሰበሰበ ኃላፊ አንቀጽ
ያንጌልግ ይሰበሰባል ትንቢት አንቀጽ
ያንገልግ ይሰበሰብ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ያንገልግ ይሰብሰብ ትእዛዝ አንቀጽ
እንገልጎ/አንገልጎት መሰብሰብ ንዑስ አንቀጽ
አንገላጊ የሚሰበስብ ሣልስ ቅጽል

 . በተንበለ ሥር የሚመደቡ ሥረይ ግሦች

ሥረይ ግሥ ትርጉም ሰዋስዋዊ ሙያ
ቀበያውበጠ ቀላወጠ ኃላፊ አንቀጽ
ይቀበያወብጥ ይቀላውጣል ትንቢት አንቀጽ
ይቀበያውብጥ ይቀላውጥ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይቀበያውብጥ ይቀላውጥ ትእዛዝ አንቀጽ
ቀበያውብጦ/ቀበያውብጦት መቀላወጥ ንዑስ አንቀጽ
ቀበያውባጢ ቀላዋጮች ሣልስ ቅጽል
ቀበያውባጢት ቀለዋጭ አንስታይ ቅጽል
ቀበያውቢጦ ቀላውጦ ቦዝ አንቀጽ
ቀንጦሰጠ ተሰለፈ ኃላፊ አንቀጽ
ይቀነጦስጥ ይሰለፋል ትንቢት አንቀጽ
ይቀነጦስጥ ይሰለፍ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይቀጦስጥ ይሰለፍ ትእዛዝ አንቀጽ
ቀንጦስጦን/ቀንጦስጦት መሰለፍ ንዑስ አንቀጽ
ቀንጦሳጢ ተሰላፊ፣ ሰልፈኛ ሣልስ ቅጽል
ቀንጦሳጢት የምትሰለፍ አንስታይ ቅጽል
ቀንጦሲጦ ተሰልፎ ቦዝ አንቀጽ
አስፌድለወ ቆጠቆጠ ኃላፊ አንቀጽ
ያስፌደሉ ይቆጠቁጣል ትንቢት አንቀጽ
ያስፌድሉ ይቆጠቁጥ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ያስፌድሉ ይቆጥቁጥ ትእዛዝ አንቀጽ
አስፌድልዎ/አስፌድልዎት መቆጥቆጥ ንዑስ አንቀጽ
አስፌድላዊ የሚቆጠቁጥ ሣልስ ቅጽል
አስፌድላዊት የምትቆጠቁጥ አንስታይ ቅጽል
አስፌድሊዎ ቆጥቁጦ ቦዝ አንቀጽ
ዜርዜቀ ነፋ፣አበጠረ ኃላፊ አንቀጽ
ይዜረዚቅ ይነፋል ትንቢት አንቀጽ
ይዜርዚቅ ይነፋ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይዜርዚቅ ይንፋ ትእዛዝ አንቀጽ
ዜርዚቆ/ዜርዚቆት መንፋት ንዑስ አንቀጽ
ዜርቂ የሚነፋ፣ነፊ ሣልስ ቅጽል
ዜርዛቂት የምትነፋ አንስታይ ቅጽል
ዜርዜቅ ወንፊት፣ የወርቅ ሀብል ዘመድ ዘር
ዜርዚቆ ነፍቶ ቦዝ አንቀጽ
ጸምሐየ ጠወለገ፣ደረቀ ኃላፊ አንቀጽ
ይጸመሒ ይጠወልጋል ትንቢት አንቀጽ
ይጸምሒ ይጠወልግ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይጸምሒ ይጠውልግ ትእዛዝ አንቀጽ
ጸምሕዮ/ጸምሕዮት መጠውለግ ንዑስ አንቀጽ
ጽምሑይ የጠወለገ፣ ጠውላጋ ሣልስ ቅጽል
ጽምሕይት የጠወለገች አንስታይ ቅጽል
ጸምሒዮ ጠውልጎ ቦዝ አንቀጽ

 . በባረከ ሥር የሚመደቡ ሥረይ ግሦች

ሥረይ ግሥ ትርጉም ሰዋስዋዊ ሙያ
ሣቀየ አሠቃየ፣አስጨነቀ ኃላፊ አንቀጽ
ይሣቂ ያሠቃያል ትንቢት አንቀጽ
ይሣቂ ያሠቃይ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሣቂ ያሠቃይ ትእዛዝ አንቀጽ
ሣቅዮ/ሣቅዮት ማሠቃየት ንዑስ አንቀጽ
ሣቃዪ የሚያሠቃይ ሣልስ ቅጽል
ሣቀዪት የምታሠቃይ አንስታይ ቅጽል
ሥቅይት የተሠቃየች አንስታይ ቅጽል
ሣቅዮ አሠቃይቶ ቦዝ አንቀጽ
ሥቃይ ጭንቅ፣ መከራ ዘመድ ዘር
ፃመወ ደከመ፣ ታከተ ኃላፊ አንቀጽ
ይፃሙ ይደክማል ትንቢት አንቀጽ
ይፃሙ ይደክም ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይፃሙ ይድከም ትእዛዝ አንቀጽ
ፃምዎ/ፃምዎት መድከም ንዑስ አንቀጽ
ፃማዊ የሚደክም ሣልስ ቅጽል
ፃማዊት የምትደክም አንስታይ ቅጽል
ፃማ ልፋት፣ጥረት ዘመድ ዘር

  . በማህረከ ሥር የሚመደቡ ሥረይ ግሦች

ሥረይ ግሥ ትርጉም ሰዋሰዋዊ ሙያ
ሰካዕለወ ቆጠቆጠ ኃላፊ አንቀጽ
ይሰካዓሉ ይቆጠቁጣል ትንቢት አንቀጽ
ይሰካዕሉ ይቆጠቁጥ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሰካዕሉ ይቆጥቁጥ ትእዛዝ አንቀጽ
ሰካዕልዎ መቆጥቆጥ ንዑስ አንቀጽ
ሰካዕላዊ የሚቆጠቁጥ ሣልስ ቅጽል
ሰካዕሊዎ ቆጥቁጦ ቦዝ አንቀጽ
ጻሕየየ አረመ፣አጠራ ኃላፊ አንቀጽ
ይጻሓይይ ያርማል ትንቢት አንቀጽ
ይጻሕይይ ያርም ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይጻሕይይ ያርም ትእዛዝ አንቀጽ
ጻሕይዮ/ጻሕይዮት ማረም ንዑስ አንቀጽ
ጻሕያዪ የሚያርም ሣልስ ቅጽል
ጻሕያይት የምታርም አንስታይ ቅጽል
ጽሕዩይ የታረመ ሳድስ ቅጽል
ጽሕይይት የታረመች አንስታይ ቅጽል
ጽሕያይ አረም፣አራሙቻ ዘመድ ዘር
ጻዕደወ ነጣ፣ጠራ፣በራ ኃላፊ አንቀጽ
ይጸዓዱ ይነጣል ትንቢት አንቀጽ
ይጻዕዱ ይነጣ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይጻዕዱ ይንጣ ትንቢት አንቀጽ
ጻዕድዎ/ጻዕድዎት መንጣት ንዑስ አንቀጽ
ጻዕዳዊ የሚነጣ ሣልስ ቅጽል
ጻዕዳዊት የምትነጣ አንስታይ ቅጽል
ጽዕድው የነጣ ሳድስ ቅጽል
ጽዕዱት የነጣች አንስታይ ቅጽል
ጽዕዳዌ ንጣት/መጥራት ዘመድ ዘር
ጸዐዳ ነጭ/ነጭማ ጥሬ ዘር
ጻዕዲዎ ነጭ ሆኖ ቦዝ አንቀጽ

 ይቆየን!

ምንጭ፡- ሰዋስው ወልሳነ ግእዝ መጽሐፍ ከገጽ ፻፰‐፻፲፬