"እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል።" ኢዮ.33፥14

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ይህ ሶፍትዌር ከዚህ በፊት 2000 .. /..አ. በ2008 / በተለቀቀው ሶፍትዌር ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች በማድረግ ማተም /ፕሪንት ማድረግ/ ንዲቻል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። ወደ ኮምፒዩተርዎ በመጫን ይጠቅሙ።

BahireHasabSetupIcon.JPG ሶፍትዌሩን እዚህ በመጫን ይጠቅሙ።

001mksebketwongel1

ዕድሜ ያልገደባቸው የኮሌጅ ተመራቂው አዛውንት

ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

003temerakiሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ቀዳሚት ሰንበት፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2007 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ ለመዘገብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተገኝቻለሁ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ዘመነ ክረምት

ሰኔ 25ቀን 2007ዓ.ም

ቀሲስ ጌትነት በቀለ (ዘአጋሮ)

የቃሉ ትርጉም ከርመ፣ ከረመ ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ወርኃ ዝናም፣ ወርኃ ነጎድጓድ፣ ዘመነ ባሕር፣ ዘመነ አፍላግ፣ ዘመነ ጠል፣ ዘመነ ደመና፣ ዘመነ መብረቅ ማለት ነው፡፡ዘመነ ክረምት ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ቀን ነው፡፡ወለእመ ፈቀድከ ታምር ክፍለ ዘመኑ ለክረምት ትዌጥን አመ እሥራ ወሰዱሱ ለሰኔ ወትፌጽም አመ እሥራ ወሐሙሱ ለመስከረም ወኊልቈ እሉ ዕለታት ተሰዓ ውእቱ እምዝ ኢየሐፅፅ ወኢይትዌሰክ ወበውስቴቶሙ ሀለው ሠለስቱ አዝማን ንዑሳን ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ፍሬ፣ ዘመነ መስቀል ይላል፡፡ (ጥዑመ ልሳን ካሳ ያሬድና ዜማው )

ዝርዝር ንባብ...
 
በሕፃናት አስተዳደግና ሥነ ምግባር ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀረበ

ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም.

ከደብረ ብርሃን ማእከል

የሕፃናት አስተዳደግና ሥነ ምግባር በሚል ርዕስ በደብረ ብርሃን ማእከል የአቡነ ጎርጎርዮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንደኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀረበ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
የዓዲ ሓቂ ግቢ ጉባኤ 22ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን አከበረ

ሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም.

ከመቀሌ ማእከል

በማኅበረ ቅዱሳን በመቀሌ ማእከል ሥር የሚገኘው ዓዲ ሓቂ ግቢ ጉባኤ 22ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በጽርሐ አርያም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ የመቐለ ማእከል አባላት፣ የግቢ ጉባኤው ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አክብሯል።

ዝርዝር ንባብ...
 
ስለ ልጄ አያሳስበኝም፡፡

ሰኔ23 ቀን 2007ዓ.ም

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

በቀዳሚት ሰንበት አመሻሹን ቤተሰብ ለመጠየቅ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ አቅጣጫ 250 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሻሸመኔ ከተማ ሄጄ ነበር፡፡ ቤተሰቤን ጠይቄ በሰንበተ ክርስቲያን ከቅዳሴ መልስ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ አደረኩኝ፡፡ከሻሸመኔ መናኻሪያ ባገኘሁት መካከለኛ አውቶብስ(€œአይሱዙ€) መጨረሻ ወንበር መሀል ተቀመጥኩ፡፡ ከተሳፋሪዎቹ አብዛኛዎቹ የዓመቱን የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚሄዱ ተማሪዎችና ልጆቻቸውን አስመርቀው የሚመጡ የተማሪ ወላጆች እንደሆኑ ተረዳሁ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 1 ከ 49