"እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል።" ኢዮ.33፥14

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ይህ ሶፍትዌር ከዚህ በፊት 2000 .. /..አ. በ2008 / በተለቀቀው ሶፍትዌር ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች በማድረግ ማተም /ፕሪንት ማድረግ/ ንዲቻል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። ወደ ኮምፒዩተርዎ በመጫን ይጠቅሙ።

BahireHasabSetupIcon.JPG ሶፍትዌሩን እዚህ በመጫን ይጠቅሙ።

001mksebketwongel1

ምሥጢሬን ላካፍላችሁ

ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም.

በአንዳንድ ዐውደ ምሕረት በማየው ችግር የተነሣ እፈተናለሁ
 
ከልጅነቴ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ጣዕሟንና ፍቅሯን ቀምሻለሁ፡፡ ትምህርቷን እንደወተት እየጠጣሁ፣ ቃሏን እንደእንጀራ እየተመገብሁ፣ ጥበቧንና ምሥጢሯን እየቀሰምሁ አድጌአለሁ፡፡ በሥራ ምክንያት ውጭ አገር ቆይቼ ወደ አገሬ ከተመለስሁ በኋላ ያንን በልጅነት ጊዜ ስሰማው የነበረውን ለዛ ያለው የእግዚአብሔር ቃል በመናፈቅ በየዓውደ ምሕረቱ እገኛለሁ፡፡ በዐውደ ምሕረት በሚሰጥ ትምህርት ስለግለሰቦች የግል ችሎታ፣ ዕውቀትና ዝና የሚነገርበትን ተደጋጋሚ ማስታወቂያ ስሰማ፣ በዚያ ላይ በሆነ ባልሆነው ዕልል በሉ፤ አጨብጭቡ የሚሉ አንዳንድ ሰባክያንን እየተመለከትሁ ዓለማዊ በሆነው የገንዘብ አሰባስብ ዘይቤ እያዘንኩ የጓጓሁለትን ቃለ እግዚአብሔር ልሰማ ባለመቻሌ ፈተና እየሆነብኝ በዚህ ችግር የተነሣ ወደ ዐውደ ምሕረቱ ለመሔድ አልገፋፋምና ምን ትመክሩኛላችሁ?

ወለተ ሥላሴ
ከአዲስ አበባ

ዝርዝር ንባብ...
 
የሰዋስወ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርትን አስመረቀ

ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

001paulosበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በብሉያት እና በሐዲሳት ትርጓሜ፤ እንዲሁም በቀንና በማታ በነገረ መለኮት ትምህርት በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 218 ደቀመዛሙርት ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አደራሽ አስመረቀ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ዕድሜ ያልገደባቸው የኮሌጅ ተመራቂው አዛውንት

ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

003temerakiሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ቀዳሚት ሰንበት፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2007 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ ለመዘገብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተገኝቻለሁ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
ዘመነ ክረምት

ሰኔ 25ቀን 2007ዓ.ም

ቀሲስ ጌትነት በቀለ (ዘአጋሮ)

የቃሉ ትርጉም ከርመ፣ ከረመ ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ወርኃ ዝናም፣ ወርኃ ነጎድጓድ፣ ዘመነ ባሕር፣ ዘመነ አፍላግ፣ ዘመነ ጠል፣ ዘመነ ደመና፣ ዘመነ መብረቅ ማለት ነው፡፡ዘመነ ክረምት ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ቀን ነው፡፡ወለእመ ፈቀድከ ታምር ክፍለ ዘመኑ ለክረምት ትዌጥን አመ እሥራ ወሰዱሱ ለሰኔ ወትፌጽም አመ እሥራ ወሐሙሱ ለመስከረም ወኊልቈ እሉ ዕለታት ተሰዓ ውእቱ እምዝ ኢየሐፅፅ ወኢይትዌሰክ ወበውስቴቶሙ ሀለው ሠለስቱ አዝማን ንዑሳን ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ፍሬ፣ ዘመነ መስቀል ይላል፡፡ (ጥዑመ ልሳን ካሳ ያሬድና ዜማው )

ዝርዝር ንባብ...
 
በሕፃናት አስተዳደግና ሥነ ምግባር ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀረበ

ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም.

ከደብረ ብርሃን ማእከል

የሕፃናት አስተዳደግና ሥነ ምግባር በሚል ርዕስ በደብረ ብርሃን ማእከል የአቡነ ጎርጎርዮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንደኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀረበ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 1 ከ 50