"እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል።" ኢዮ.33፥14

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ይህ ሶፍትዌር ከዚህ በፊት 2000 .. /..አ. በ2008 / በተለቀቀው ሶፍትዌር ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች በማድረግ ማተም /ፕሪንት ማድረግ/ ንዲቻል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። ወደ ኮምፒዩተርዎ በመጫን ይጠቅሙ።

BahireHasabSetupIcon.JPG ሶፍትዌሩን እዚህ በመጫን ይጠቅሙ።

ማኅበረ ቅዱሳን በትግራይ ሦስት ገዳማት የተገበራቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ

 ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.


በእንዳለ ደምስስ

gundagundi 02ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት አማካይነት በምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት በደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዲ ቅድስት ማርያም፤ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት በአስገደ ጽምባላ ወረዳ በአቡነ ቶማስ ደብረ ማርያም ዘሃይዳ፤ በምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት በማቅናት አጽቢ ወምበርታ ወረዳ በደብረ ቅዱሳን ዲቦ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳማት ያከናወናቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
ህዳር 8/2007 ዓ.ም
 

የሰው ልጅ በገነት እንደ ቅዱሳን መላእክት በቅድስና አምላኩን በማመስገን በደስታ ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን “ክፉና ደጉን ከምታሳውቀው ዕፀ በለስ እንዳትበላ” ተብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ከአምላኩ ተለየ(ዘፍ.3፡6)፡፡እግዚአብሔር በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረው ሰው ክብሩን አጣ፣ ጸጋው ተገፈፈ፣ ፈጣሪውንም አሳዘነ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረው ሰው ከክብሩ ተዋርዶ ሲመለከቱ ተከዙ፡፡

 

የሰው ልጅ ጠፍቶ እንዲቀር ያልወደደው እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ለማዳን ራሱን ዝቅ አድርጎ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ተወለደ፡፡ቅዱሳን መላእክትም ከላይ ከአርያም ከአባቱ ሳይለይ እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ለማዳን ሲል በግዕዘ ሕፃናት ተወልዶ፣ በእናቱም እቅፍ ሆኖ፤ እንስሳት እስትንፋሳቸውን እያሟሟቁት በማየታቸው ተደነቁ፡፡ ሰውን ለማዳን ሲል ራሱን ዝቅ በማድረግ የባርያውን አርአያ እንደነሣ አስተውለው “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት፣ ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” (ሉቃ.2፡14) ብለው አመሰገኑት፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
የማቴዎስ ወንጌል

ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.

ምዕራፍ 10

ባለፉት እትሞቻችን የማቴዎስን ወንጌል እስከ ምዕራፍ ዘጠኝ ያለውን በአባቶቻችን ትርጓሜ ምን እንደሚመስል በዝርዝር ስንመለከት ቆይተናል፡፡ ይህንንም ያደረግነው የትርጓሜ መጻሕፍትን ጥቅም ዐውቀን በንባብ ብቻ ከመነዳትና ከመሰናከል ተጠብቀን እንድንጓዝ፣ ከአባቶቻችንም መጻሕፍት ጋር እንድንተዋወቅ ነው፡፡ መንገድ ለማሳየት ያህል ዘጠኝ ምዕራፎች በዝርዝር ከተመለከትን የተቀሩትን ደግሞ ጠቅለል ባለ መልኩ እናቀርባለን፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
በአንድ ባለ ሀብት የተሠራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተመረቀ

ኅዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም.


በእንዳለ ደምስስ

haro 01በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጪ ወረዳ በአንድ ባለ ሀብት የተሠራው የሀሮ ቅዱስ በዓለ ወልድ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትየጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኅዳር 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመረቀ፡፡

ዝርዝር ንባብ...
 
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቀባበል ተደረገላቸው

 መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ 

ህዳር 09 ቀን 2007 ዓ.ም.

በ2007 ዓ.ም የጥቅምት ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ሥራ ለመጀመር ከሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች፣ ከአጥቢያ ገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች፣ ጸሐፊዎችና ምእመናን ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

 

ብጹዕነታቸው የሥራ መጀመሪያቸው ለሆነው የትውውቅ መርሐ ግብር ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲሔዱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  ለጉባኤው ታዳሚዎች ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳን ‹‹እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› በሚለው ቃለ ወንጌል የቅድስና ሥራ መሥራት እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

 

ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የፍቼ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስም ‹‹ለሁለት ጌታ፤ ለገንዘብና ለእግዚአብሔር መገዛት አንችልም፡፡ ለገንዘብ ስንገዛ የኖርንበትን ዘመን ትተን እስቲ ለእግዚአብሔር እንገዛ›› በማለት አባታዊ መልእክታቸውን ለጉባኤው ታዳሚ አስተላልፈዋል፡፡

 

አዲሱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስም  የሀገረ ስብከቱን ሠራተኞችንና ሌሎች የአጥቢያ ባለጉዳዮችን በጽ/ቤታቸው ብቻ እንደሚያስተናግዱ ገልጸዋል፡፡

 


                    ለብፁዕነታቸው መልካም የሥራ ዘመን እንመኛለን፡፡

 

 

 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 1 ከ 7