- (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፳፫) -
"ወንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ"
እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን
- (ሉቃ ፩፥፳፰) -
"ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ "
መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
ቅዱሳን አባቶች
ሥራህን ሥራ
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ።በእርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን ኦንዲጠይቁህ እጅግ
ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ፥ሄሮድስ፥ሐናንያ፥ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በጸና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።
አባ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፩፱፫፪፡፩፱፰፪ ዓ.ም.
አዳዲስ ዜናዎች እና ክንውኖች
ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ባለፉት ሁለት ክፍሎች ‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ›› በሚል ርእስ ጽሑፍ አድርሰናችኋል፡፡ አንብባችሁ ቁም ነገር እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ አሁን ደግሞ ክፍል ሦስትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ መልካም ንባብ!
ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ባለፈው ሳምንት ‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ›› በሚል ርእስ ባቀረብንላችሁ ጽሑፍ ቤተ ክርስቲያን ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዴት እየተላለፈች ወደ እኛ እንደደረሰችና እኛም እንዴት ከአባቶቻችንና እናቶቻችን እንደተረከብናት በጥቂቱ የዳሰስንበትን ክፍል አድርሰናችኋል፡፡ በዚህ በክፍል ሁለት ደግሞ ከክፍል አንድ የቀጠለውንና “ቤተ ክርስቲያንን እኛስ እንዴት ለቀጣዩ ትውልድ እናስተላልፋት?፡ የሚለውን ክፍል ይዘንላችሁ ቀርበናል፤…
ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ቃል የተናገረው ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው መልእክቱ ነው፡፡ ዕለት ዕለት ጽኑ የሆኑ መከራዎች ያጋጠሙት ቢሆንም ያ ሁሉ ሳያሳስበው፣ ሳይከብደውና ሳያስጨንቀው በመዓልትም በሌሊትም ዕረፍት የሚነሣው የቤተ ክርስቲያን ነገር ነበር፡፡ የተጠራው ለቤተ ክርስቲያን እንዲያስብና እንዲያገለግል በመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ የደረሱበትን ችግሮች ሁሉ ገለጸላቸው፡፡
ውድ አንባብያን! የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ቤተ ክርስቲያን ምንነት፣ ታሪክ ወዘተ መተንተን አይደለም፡፡ የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ምን መምሰል አለባት? እንዴትስ ለትውልዱ እስከ ክብሯና ግርማ ሞገሷ ትሻገር? የሚለውን አሳሳቢ ጉዳዮችን መዳሰስ ነው እንጂ፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? የግማሽ ዓመት ትምህርት ተጀምሯልና በደንብ ትኩረት ሰጠታችሁ መማር ይገባል! ልጆች! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ! በባለፈው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን “ሃይማኖት” በሚል ርእስ ተምረን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለ “ሀልዎተ እግዚአብሔር” ማለትም ዓለምን ሁሉ የፈጠረ የአምላካችን የእግዚአብሔር መኖር በምን እንደሚታወቅ እንማራለን፤ ተከታተሉን!
የቤተ ክርስቲያናችን አስተዋጽኦ የሚገለጠው “እንዴት አሸነፍን?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ስንመረምር ነው፡፡ ይህ ዓለምን በብርቱ ጠፍንጎ የያዘና አንዱን ባሪያ ሌላውን ጌታ የሚያደርግ፣ ሰውን ያህል ፍጡር እንደ ከብት ነድቶ፣ እንደ ዕቃ ጎልቶ፣ ለገበያ አቅርቦ የሚሸጥ እኩይ አስተሳሰብ ከመሠረቱ የናደ፣ ነጻነት ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ለሌሎች ያሳየ፣ የአስተሳሰቡ ሰለባ የነበሩ ነጮችንም ያስደነገጠ…
ማኅበሩ በመግለጫው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መንፈሳዊ አንድነት የጠየቀ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም" የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን "አንዳንድ አባቶች" ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ጉዳዩንም በመከታተል መረጃውን ለምእመናን አደርሳለሁ ብሏል።፡፡
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
ወንህነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ፣ እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን