‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ›› (መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፥፩)

በብሥራተ መልአክ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችውን አንድያ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት በፈለገው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዷን የሚያመለክተውን፣  ከስደትም እንድትመለስ ጠቢቡ በትንቢት ቀድሞ የተናገረው ይህን ቃል ነው፡፡ ወቅቱ አብዝተን ስለ ስደቷና ተያያዥ ታሪኮች የምንማርበት፣ የምንጸልይበት፣ የምናስተምርበትና የምንዘምርበት ወቅት በመሆኑ በዚህ ርእስ ተከታታይ ጽሑፎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፤ ተከታተሉን!

‹‹በደስታ በዓልን አድርጉ›› (መዝ.፻፲፯፥፳፯)

ቀናትን ሁሉ ባርኮ የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ጊዜ የእርሱ ስጦታ በመሆኑ የከበረ ድንቅ ሥራውን ፈጽሞበታል፡፡ በእያንዳንዱ ዕለት ፍጥረታትን ከመፍጠሩ ባሻገር ለምስጋና፣ ለውዳሴ እና ለድኅነት ያከበራቸው በዓላትም አሉት፤ በእነዚህ ዕለታት ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡

ቅዱስ መስቀል

ቅዱስ መስቀል ቀስት ከተባለ ጠላታችን ዲያብሎስ እንድናመልጥና ድል እንድናደርገው የተሰጠን ነው፤ ቅዱስ መስቀል መድኅን ዓለም ክርስቶስ ተሰቅሎ በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን፣  ሰላማችን የታወጀበት ኃይላችን፣ የሰላም አርማችን ነው!

ርእሰ ዐውደ ዓመት

የዘመናት አስገኝ፣ የፍጥረታት ባለቤት፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ዓመታትን በቸርነቱ የሚያፈራርቅ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ  በቸርነቱ አሻግሮናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን!

በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል

በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል በጳጉሜን ሦስት ቀን የሚዘከር በዓል ነው፡፡ “ሩፋኤል” የሚለው ስያሜ ትርጉም “ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ” ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከዕብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት የተገኘ ቃል ነው፡፡ “ሩፋ” ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን “ኤል” ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጸል ስመ አምላክ ነው::

“ተዘጋጅታችሁ ኑሩ’’ (ማቴ.፳፬፥፵፬)

ጌታች አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ የነገራችው ኃይለ ነው፤ ‘’ጌታችሁ በምን ሰዓት እንደሚመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ፤ እወቁ ባለቤት ሌሊት ሌባ በየትኛው ጊዜ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ፤ ቤቱንም እንዲቆፈር ባልተወ ነበር’’ አላቸው፡፡ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ይመጣልና፤

“ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” (መዝ.፻፲፭፥፭)

ተክለ ሃይማኖት ማለት የስሙ ትርጓሜ “የሃይማኖት ተክል ማለት” ነው። ተክል ሥርም፣ ግንድም፣ ቅጠልም፣ ቅርንጫፍም ነውና ተክለ ሃይማኖት እንጂ ሌላ አላላቸውም። በእርሳቸው ተክልነት ቅርንጫፍ የሆኑ ፲፪ ከዋክብት አሉና “ተክል” አላቸው። ተክል ባለበት ልምላሜ አለ፤ እርሳቸው ባሉበትም የኃጢአት ፀሐይ፣ የርኩሰት ግለት የለም፤ የጽድቅ ዕረፍት እንጅ። ተክል ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ተደግፎት ይኖራል! ቢቆርጡት ለመብል ለቤት መሥርያ ይሆናል፤ ቢያቆዩት ማረፊያ መጠለያ ይሆናል፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በዐጸደ ነፍስ ሆነው በምልጃ በጸሎት ያግዛሉ፤ ያማልዳሉ፤ በሕይወት ሳሉም በትምህርታቸውና በተአምራታቸው ኃይል ለብዙዎች ዕረፍት ሰጥተዋል።

“ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ!”

መኮንኑ አፈረና ጽኑ ሥቃይ ሊያሠቃያቸው ወድዶ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ድምፅ ወደ ሚያስተጋባው የፈላ ውኃ እንዲጥሏቸው አዘዘ፤ ያን ጊዜ እናቱ ፈራች፤  ሕፃኑ ግን ለእናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እንዲህም አላት፤ “እናቴ ሆይ አትፍሪ! ጨክኝ፤ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል” አላት። እናቱ ቀና ብላ ብትመለከት ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁትን የብርሃን ማደርያቸውን ተመለከተች፤ ደስም ተሰኝታ እንዲህ አለች፤ “ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ፤ እኔም ልጅህ ነኝ፤ አንተን የወለድኩባት ቀን የተባረከች ናት፡፡”

‹‹ሐሰትን አትነጋገሩ›› (ሌዋ.፲፱፥፲፩)

ከሁሉም አስቀድሞ ሰዎች ፈጣሪ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ እንደሆነ ልንረዳ ይገባናል፡፡ እርሱ እውነተኛና የእውነት መንገድ እንደሆነ ስንናውቅ መንገዳችን በእውነትና ስለ እውነት ይሆናል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ›› በማለት እንደተናገረው በሕይወታችን ውስጥ እውነትን ማሰብ፣ እውነትን መናገር እንዲሁም በእውነተኛው መንገድ መጓዝ የሚቻለን አምላካችን እውነተኛ መሆኑንና ሐሰትን እንደሚጠላ ስናውቅ ነው፡፡ (ዮሐ.፲፬፥፮)

ነጻነት

ነጻነት ከሰው ልጅ አፈጣጠር ጋር የተያያዘ ግብር መሆኑን ማወቅ እጅጉን ተገቢ ነው። አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በአርአያውና በአምሳሉ ሲፈጥረው ሙሉ ነጻነት ያለው ፍጥረት አድርጎ ነው፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ በተሰጠው አእምሮ የወደደውን (ክፉውን ከሻተ ክፉውን፣ መልካሙን ከሻተ መልካሙን) እንዲመርጥ የመምረጥ መብት ተሰጥቶታል።