«የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው» /ሉቃ. ፩፥፶፫/

በፍጡራን አንደበት ተነግሮ ስለማያልቅ ክብሯና ልዕልናዋ ክብር ምስጋና ይድረሳትና ይህንን ኀይለ ቃል የተናገረችው አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ወንጌላዊው ሉቃስ በወንጌሉ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን እንደ ጻፈልን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ኀይለ ቃላት ያላቸውን ምሥጢራት በዚህ ክፍል ተናግራለች። ይህ የተናገረችው  ኀይለ ቃል በውስጡ ብዙ መንፈሳዊ፣ ሰማያዊ ትርጉም አለው። ምልእተ ጸጋ፣ምልእተ ውዳሴ፣ምልእተ ክብር የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ የጸሎት ክፍል ከተናገረችው ብዙ ወርቃማ ቃላት  መካከል ለትምህርታችን «የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው» የሚለውን ኃይለ ቃል እንመለከታለን። ይህንን ኀይለ ቃል እመቤታችን ስለ ሦስት ነገር ተናግራዋለች፤ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው።

‹‹መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ምትሐት ምስሎአቸው ታወከው በፍርሃት ጮኹ።  ጌታችን ኢየሱስም ‹‹አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ አትፍሩ›› አላቸው፤  ቅድስ ጴጥሮስም መልሶ፥ አቤቱ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ›› አለው። እርሱም ‹‹ና›› አለው። ጴጥሮስም ከታንኳው ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ።  ነገር ግን ነፋሱ በርትቶ ባየ ጊዜ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ወዲያውም ጌታችን ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘው ‹‹አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ?›› ብሎታል፡፡ መጠራጠር ያለመጽናት፣ ያለማመን ውጤት ነውና፡፡ (ማቴ. ፲፬፥፳፬-፴፩)

‹‹ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ›› (ዮሐ. ፲፬፥፳፯)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ለሕዝቡ ‹‹ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ…›› ብሎ በነገራቸው ቃሉ ሰላምን የሚሰጠው እርሱ እንደሆነ እንረዳለን፤  ይህም የተወልን ሰላም መንፍሰ ቅዱስ በመሆኑ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ውስጥ ሲያድር የልብ ሰላምን ይጎናጸፋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ሰላም ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፤‹‹አእምሮውንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና ሀሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል፤›› (ዮሐ. ፲፬፥፳፯፤ ፊል. ፬፥፯)

‹‹እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው›› (ዕብ. ፲፩፥፩)

ማንኛውም የሕይወት ውጣ ውረድ ቢያጋጥመን በእምነት ከጸናን የማናልፈው ነገር የለም፡፡ የማንዘለው የችግር እና የመከራ ግንብ፣ የማንሻገረው ባሕር እና መሰናክል አይኖርም፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር ከኖርን የሚያስፈራን አንዳች ነገር አለመኖሩን ሲያስረዳ ‹‹በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሔድ፤ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል›› ብሏል፡፡ (መዝ. ፳፪፥፬)

‹‹ድኀነት››

የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ያጣውን የተፈጥሮ ጸጋ ክብር በአዲስ ተፈጥሮ እንደገና ለመታደል መብቃቱን ለመግለጽ የሚነገር ልዑል ቃል ‹‹ድኀነት›› ነው፡፡ ድኀነት የሚለው ቃል አዳም በክርስቶስ የታደለውን የሕይወተ ሥጋና ሕይወት ነፍስ፣ በረከተ ሥጋና በረከተ ነፍስ ጸጋ ወይም በሌላ አነጋገር የሞተ ሥጋና የሞተ ነፍስ ድቀት የደረሰበት አዳም በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘው ትንሣኤውና ሕይወት የሚገለጽበት ሕያው ቃል ነው፡፡

“ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ትንቢተ ዮናስ ፪፥፲)

እግዚአብሔር ከበሽታ ይፈውሳል፤ ከችግርና መከራም ይሰውራል፡፡ በየጸበል ቦታው ተጠምቀው ከኤች አይ ቪ፣ ከካንሰር እና ከሌሎች በሽታዎች የተፈወሱ ሰዎች እንዳሉ ዓይናችን እንዲሁም የሕክምና ማስረጃዎች ምስክሮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ኃያል አምላክ፤ ሥራውም ድንቅ ነው፤ ተአምራትንም ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ከእርሱ ለማግኘት እምነት ያስፈልጋል፡፡

“የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” (ገላ. ፮፥፪)

የክርስቶስ ሕግ ፍጻሜ ፍቅር ነው። ፍቅር አንድ ሰው ከሌላው ጋር በየዕለቱ የሚያደርገው ግንኙነት፣ በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ልባዊ መዋደድና ጥልቅ መንፈሳዊ ጸጋ ነው። በሰዎች መካከል በሚኖረው መልካም ግንኙነት የተነሳ አንዱ ለሌላው የሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ ፍቅር ነው።

“ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” (ሉቃ.፩፥፵፰)

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምናመሰግናት ስለተሰጣት ጸጋ እና ክብር ነው። የተሰጣት ክብር ደግሞ ከጸጋ ባለቤት ከልዑል እግዚአብሔር መሆኑን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ስለ ተሰጣትም የእግዚአብሔር ጸጋ የሔዋን መርገም በእርሷ ላይ ተቋረጠ እንዲህ ያለ ስጦታ ለአዳም እና ለዘሩ እስከ ዘለዓለም ለሌላ አልተሰጠም።›› በዚህ ብቻ ሳይሆን ስለ ንጽሕኗዋ፣ ስለ ቅድስናዋ ጭምር ምስጋና እናቀርባለን ።

“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ቅዱስ ያሬድ)

በመጻሕፍት አምላካውያት (አሥራው መጻሕፍት) እና በሊቃውንት አበው አስተምህሮ የተነገሩ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናዋን ቅድስናዋን የሚመሰክሩ መውድሳት ቅኔያትና ዝማሬያት እንዲሁም በሰፊው የተገለጡትን ምስክርነቶች ስንመለከት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ የተገኙ እንዳልሆነ አስተዋይ ሰው በቅጥነተ ሕሊና ቢረዳው የሚያውቀው እውነት ነው፡፡

“ኦሪትና ነቢያት በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ጸኑ” (ማቴ.፳፪፥፵)

መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በተናገረው በዚህ ኀይለ ቃል ፍቅር የሁሉም ነገር ማሰሪያና መደምደሚያ መሆኑን እንማራለን፡፡ ሰው የሕግ ሁሉ ማሰሪያ የሆነውን እርሱም ፍቅርን ገንዘብ ሊያደርግ እንደሚገባ ያስረዳበት አማናዊ ትምህርት በመሆኑም ሁሉም ሊያውቀውና ሊረዳው እንዲሁም በተግባር ሊፈጽመው የሚገባ ነው፡፡