Entries by Mahibere Kidusan

  የ፳፻፲፩ ዓ.ም የአጽዋማት ባሕረ ሐሳባዊ ቀመር

በዲ/ን ታደለ ሲሳይ በዘመናት ሁሉ የነበረው ያለውና የሚኖረው፣ ሁሉን የፈጠረ በሁሉም ያለ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ በዚህን ጊዜ መኖር ጀመረ፣ በዚህን ጊዜ መኖር ያቆማል የማይባልለት የህልውናው መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ ነው፡ “ተራሮች ሳይወለዱ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ ከዘላለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነህ”፡፡ “ኢየሱስም እውነት እውነት እላችኋለሁ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው፡፡”፣ ብሏል፡፡ በተጨማሪም፣ “ኢየሱስ […]

በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተከሰተው ችግር ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰጠ መግለጫ!

                                                                 እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል /ሮሜ  14፥19/ ።          በሀገራችን በኢትዮጵያ የሚካሔደውን የመንግሥት የአሠራር ለውጥ ተከትሎ ላለፉት ጥቂት […]

ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም የተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በአባቶች ላይ በተለያየ ወቅት ያስተላለፈውን ቃለ ውግዘቱን አንስቷል

ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም የተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በአባቶች ላይ በተለያየ ወቅት ያስተላለፈውን ቃለ ውግዘቱን አንስቷል፡፡ሙሉ ውሳኔው እንደሚከተለው ነው

   የአባቶች አንድነት ላይ የተሰጠ  የደስታ መግለጫ!

        ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ ከእቶነ እሳት በወጡበት በብሥራተ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል የመታሰቢያ ዕለት የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  አባቶች  አንድ ሆነዋል፡፡በዚህም የምእመናን ተስፋ ለምልሟል፡፡የጥል ግድግዳ ፈርሷል፡፡ይህ ታላቅ መንፈሳዊ ተግባር የተፈጸመበት ዕለት ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ የደስታ ዕለት ነው፡፡ይህ ዕለት ሰይጣን ቤተ ክርስቲያንን ለመዋጋት ጥይቱን የጨረሰበት፤ዝናሩን አራግፎ ባዶ እጁን የቀረበት ነው፡፡ዕለቱ የሰይጣን ጥርሱ […]

የአባቶች ዕርቀ ሰላም መፍጠር፤ ለቤተ ክርስቲያንሐዋርያዊ አገልግሎትና ለሀገራዊ መግባባት ወሳኝ ሚና አለው!

  በዮሐንስ አፈወርቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሠረቷኗ ጉልላቷ ክርስቶስ በመሆኑ የሰላም ደጅ ናት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ በጻፈው መልእክቱ “የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ፡፡ ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡” (2ኛ ተሰሎ 3፡16) እንዳለ በክርስቶስ ሰላም እየተጠበቀች አንድነቷ ላይ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች ሁሉ እየተቋቋመች አገልግሎቷን በማስፋፋት ምእመናንን ትጠብቃለች፡፡ አባቶችም ከቤተ ክርስቲያን የተቀበሉትን አደራ ተግተው በመጠበቅ መንጋውን […]

ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ Mahibere Kahinat North America

                              ከሁሉ አስቀድመን እኛ የመንፈስ ልጆቻችሁ ካለንበት ከሰሜን አሜሪካ ሆነን ቡራኬአችሁ ይድረሰን እንላለን! ውድ አባቶቻችን የታላቋ ቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ላለፉት ከሃያ ዓመታት በላይ ለሁለት መከፈል ምክንያት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የደረሰውን ውድቀት በእኛ በመንፈስ ልጆቻችሁ ካህናት እንዲሁም ምዕመናን ላይ የደረሰውን ሐዘን ታላቅነት […]

በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃ ለማድረግ እና ሰላምና አንድነትን ማምጣት እንዲቻል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምር ለ2000 ዓመታት አንድነቷን፣ ዶግማዋንና ቀኖናዋን ጠብቃ የቆየች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት የውጭና የውስጥ ፈተናዎች ቢፈራረቁባትም ፈተናዎቹን በመቋቋም፣ እምነቷን በማጽናት፣ ቀኖናዋንና ትውፊቷን በመጠበቅ፣ ተከታዮቿን በመምከርና በማስተማር ሀገርን ሰላም እያደረገች ኖራለች፡፡ ሆኖም በ1984 ዓ.ም. የነበሩት […]