፲፫ኛው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ሊካሔድ ነው

የማኅበረ ቅዱሳን ፲፫ኛው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሜታ አቸኒ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እሑድ ታኅሣሥ ፲፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም (ታኅሣሥ 15 ቀን 2010 ዓ.ም) ይካሔዳል፡፡

በመርሐ ግብሩ፣ ትምህርተ ወንጌል እና ምክረ አበው በመምህራነ ቤተ ክርስቲያን ይሰጣል፡፡ ያሬዳዊ ዝማሬያትም በማኅበሩ እና በተጋባዥ ዘማርያን ይቀርባሉ፡፡

በዚህ ጉዞ በመሳተፍ ነፍሳችሁን ቃለ እግዚአብሔር መግቡ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ግብዣ አቅርቦላችኋል፡፡

  • ስለጉዞው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በሚከተሉት ስልክ ቍጥሮች በመደወል መጠየቅ ይቻላል፤

09 44 71 82 82

09 44 71 82 83

09 11 89 89 90

ማኅበረ ቅዱሳን